49ኛዉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ትርኢት በበርሊን | ዓለም | DW | 04.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

49ኛዉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ትርኢት በበርሊን

ኤግዚቢሽኑ ከ60 በላይ አገራትን በማሳተፍ ላይ ሲሆን 1164 ያህል የተለያዩ ድርጅቶች፣ የተለያዩ አዳዲስ ስራዎቻቸዉን ማቅረባቸዉ ተገልጾአል

default

ዛሪ በበርሊን 49ኛዉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ትርኢት በመታየት ላይ ነዉ ። ይህ ለስድስት ቀናት የሚዘልቀዉ የተለያዩ ድንቅ ኤሌክትሮኒክስ ግኞች የሚታዩበት ኤግዚቢሽን ከ60 በላይ አገራትን በማሳተፍ ላይ ሲሆን 1164 ያህል የተለያዩ ድርጅቶች፣ የተለያዩ አዳዲስ ስራዎቻቸዉን ማቅረባቸዉ ተገልጾአል። ትናንት አመሻሽ ላይ በመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ተመርቆ የተከፈተዉን በአለማችን ድንቅ የተባለለትን ይህን የኤሌክትሮኒክስ ትርኢት ዛሪ የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ሃይለሚካኤል ጎብኞታል።

Audios and videos on the topic