ፖለቲካእስያ
40 ቀኑን የያዘው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት
ሰኞ፣ መጋቢት 26 2014ማስታወቂያ
ካልተጠበቀው የዓለም ክፍል ባልተጠበቀ ሰዓት የፈነዳው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ 40 ቀን ሞላው። በእነዚህ 40 ቀናት በርካታ የዩክሬን ከተሞች ወድመዋል፤ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሞተዋል፤ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ተሰደዋል ወይም ከመኖሪያ ቤት አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። የተመድ እንደሚለው ከሀገር ውጪ የተሰደዱት ቁጥራቸው ከአራት ሚሊየን አልፏል። ጦርነቱ ሩሲያ ዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ቢሆንም ብዙዎች ግን ከዩክሬን ጀርባ ምዕራብ ሃገራት እንዳሉ በመጥቀስ ዓለም በሁለት ጎራ ተከፍሎ እንደሚፋለም ነው የሚቆጥሩት። ማኅደረ ዜና 40 ቀኑን የያዘው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከውድመት ኪሳራው ባሻገር በዓለም አቀፍ እና የኃይል አሰላለፍ አኳያ ያለውን ተጽዕኖ ይመለከታል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ