3ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተከሳሾች እና ብይናቸው | ዓለም | DW | 12.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

3ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተከሳሾች እና ብይናቸው

በመላ ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስራ አክባሪነታቸው እና በጨዋነታቸው ነው የሚታወቁት። ሰሞኑን ከወደ ዩ ኤስ አሜሪካ የመጣው ዜና ግን የዚህ ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቶዋል።

በዋሽንግተን በሚገኘው የአየር እና የኅዋ ቤተ መዝክር በሆነው በስሚዝሶንያን ሚውዝየም የአውቶሞቢል ማቆሚያ ሥፍራ ወይም ፓርኪንግ ሎት ይሰሩ የነበሩ ሦስት ትውልደ ኢትዮጵያውያን፡ ማለትም፡ ሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ፡ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ዶላር በላይ አጭበርብረዋል በሚል ተከሰው ጥፋተኛ መሆናቸው ተረጋግጦባቸዋል። ሁለቱ የእሥራት ቅጣት እና የወሰዱትን ገንዘብ እንዲከፍሉ ሲፈረድባቸው አንዷ ብይኑ ሳይሰጥ በፊት ሕይወቷን አጥፍታለች። እነዚህ ሦስት ግለሰቦች በስንት ዓመት ይህን ያህል ገንዘብ ከድርጅቱ ሊያጭበረብሩ ቻሉ? በምን ዓይነት ዘዴስ ተጠቀሙ?

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic