26ኛ ዓመት፤ ዲሞክራሲ ወይስ ዉዝግብ? | ኢትዮጵያ | DW | 29.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

26ኛ ዓመት፤ ዲሞክራሲ ወይስ ዉዝግብ?

በ26ኛ ዓመቱ ዘንድሮ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰማንያ ሰባት ወደ 547 መቀመጫ ሰፍቷል።ሁሉንም መቀመጫ የሚቆጣጠሩት ግን ኢሐዴግ እና ስድስት ተባባሪዎቹ ወይም አጋር የሚላቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸዉ።ትናንት የተከበረዉ የግንቦት 20 በዓልም ለተቃዋሚ ፓርቲዎች፤

አውዲዮውን ያዳምጡ። 17:14

ዲሞክራሲ ወይስ ዉዝግብ?

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን የያዘበት 26ኛ ዓመት ተከበረ።የደረግ ዉድቀት የሠላም፤ የዴሞክራሲ፤ የፍትሕ ጭላንጭል፤ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ጅምር  ነዉ ተብሎ-መስሎም ነበር።በሃያ ስድስተኛ ዓመቱ ዘንድሮም ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በከፊል ገና ሥለ ዴሞክራሲ ይደራደራሉ። በከፊል ይወዛገባሉ። ምክንያቱ ብዙ፤ ለየቅልም። ጥቂቱን አንቃኝ።                               
ሰኔ 1983 ተሰይሞ በነበረዉ የሽግግር መንግሥት መሥራች ጉባኤ ላይ ከ20 በላይ  የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዉ ነበር።ጉባኤዉ የሠመዉ የሽግግር ምክር ቤት 87 መቀመጫዎች ነበሩት። በዚሕ ምክር ቤት ዉስጥ በጉባኤዉ የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ዉክልና ነበረቸዉ።በ26ኛ ዓመቱ ዘንድሮ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰማንያ ሰባት ወደ 547 መቀመጫ ሰፍቷል።
ሁሉንም መቀመጫ የሚቆጣጠሩት ግን ኢሐዴግ እና ስድስት ተባባሪዎቹ ወይም አጋር የሚላቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸዉ።ትናንት የተከበረዉ የግንቦት 20 በዓልም ለተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዳሉት ከመስከረም ሁለት የተለየ አይደለም።
                            
ስምንት የፖለቲካ ፓርሪዎችን የሚያስተናብረዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ባጭሩ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር

በየነ ጴጥሮስ «ነፃነት በሌለበት ነፃ መሆን ይቻላል?» ጠየቁ-ለጥያቄዬ መልስ።የኢሕአዲግ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሺፈራዉ ሽጉጤ ግን ኢሕአዴግ ለፍትሕ ዴሞክራሲ የታገለዉ ዛሬ አይደለም ይላሉ።

                      
የመብት ተሟጋቾች ግን ከዚሕ በተቃራኒዉ ኢሕአዴግን  በሰብአዊ መብት ረጋጭነት፤ በምባገነንነት በአፋኝነት እየተወቀሱት ነዉ።በአደባባይ ሠልፍም ሕዝብ እያወገዘ፤ እየወቀሰ እየተቃወመዉ ነዉ።ከተደጋጋሚዉ ዉግዘት፤ ወቀሳ፤ ሠልፍ በኋላ ኢሕአዴግ ከ21 ተቃዋሚዎቹ ጋር የጀመረዉ ድርድር ምናልባት የፖለቲካ ሥርዓቱን በመጠኑም ቢሆን ለማስፋት ይረዳል የሚል ተስፋ ፈንጥቆ ነበር።ባለፈዉ ጥር አስር የተጀመረዉ ድርድር ዛሬ  ያለበት ደረጃ ግን እንደየፖለቲከኞቹ እይታ አለ፤ የለምም መባሉ እንጂ ዚቁ።
                            
ድርድሩ ገና ከጅምሩ ከትችትና ተቃዉሞ አላመለጠም።የተቺ ተቃዋሚዎቹ ምክንያት ብዙ ነዉ።የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት እንደታሰሩ፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይጋበዙ የሚደረግ ድርድር ትክክለኛ ዉጤት አያመጣም የሚለዉ አንዱ ነዉ።ኢሐአዴግ ድርድሩን በዚሕ ወቅት የጠራዉ የተነሳበትን ሕዝባዊ ተቃዉሞ እና ጫና ለማርገቢያነት ሊጠቀምበት እንጂ የፖለቲካ ሥርዓቱን ለማሻሻል ፈልጎ አይደለም የሚለዉ ሁለተኛዉ። የኢሕአዴግ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሺፈራዉ ሽጉጤ ሁለቱንም አይቀበሉትም።
                                         
በርግጥም

መሪዎቻችን ታስረዉ አንደራደርም ያለ የፖለቲካ ፓርቲ የለም።21ዱም በድርድሩ ተካፍለዋል።ሁለቱ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ግን አቋርጠዉ ወጥተዋል።ምክንያት አንድ፣« ኢሕአዴግ መጀመሪያዉኑ መቼ ለድርድር ቀረበና» ይላሉ- የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ።
                                        
የመጀመሪያዉ ግልፅ ሆነ።አቶ ሽፈራዉም የተቀበሉት መስለዋል።ግልፅ ያልሆነዉ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ከድርድሩ የወጡበት ምክንያት ነዉ።እንደገና አቶ ሺፈራዉ።
                                
የመድርክ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እሁለት የሚከፈል መልስ አላቸዉ። የመጀመሪያዉ ድርድሩ በትክክል የሕዝብን ጥያቄ መመለስ አለበት የሚል ነዉ።
                                 
ሁለተኛዉ ምክንያት ድርድሩ ትክክለኛ ዉጤት እንዲያመጣ መድረግ የሌሎቹን ዉክልና ካገኘ ከኢሐድግ ጋር ይደራደር የሚል ነበር።ይሕን ሲል  ትልቅ ፓርቲ በመሆኑ ለብቻዬ ልደራደር አላለም ባይ ናቸዉ ፕሮፌሰር በየነ።
                                 
የመድረክ ምክንያት ሰወስት ነዉ።ፕሮፌሰር በየነ እንዳሉት።የሰማያዊስ?  የፓርቲዉ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ምክንያቱን ይነግሩናል።                        
               
የኢሕአዲግ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ መልስ አላቸዉ።
                             
እንደገና አቶ የሺዋስ።

ከእንግዲሕስ? መድረክ
                         
ሰማያዊ ፓርቲ
           
ኢሕአዴግ  

          
ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ

      

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች