1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ

ዓርብ፣ ጥር 8 2012

መንግስት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን ትኩረት አድርጎ በመስራቱ  238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ከጥር 6 እስከ 11 ባሉት ተከታታይ ቀናት  238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።

https://p.dw.com/p/3WMdq
Äthiopien | Außenministerium | Pressekonferenz
ምስል S. Muchie

የህዳሴ ግድብ የተካሄዱት የቴክኒክ ምክክሮች አንዱ የመግለጫዉ አካል ነዉ

መንግስት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን ትኩረት አድርጎ በመስራቱ  238 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከጥር 6 እስከ 11 ባሉት ተከታታይ ቀናት  238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ። ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በመግለጫዉ የኢትዮ-ጅቡቲ የጠረፍ አስተዳደሮች የድንበር ደህንነት ትብብር መፍጠር፣ ሕገ ወጥ ዝውውርን መከላከል እንዲሁም በሃገራቱ መካከል የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በተመለከተ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። መግለጫዉ የኢትዮ- ቻይና ዲፕሎማስያዊ ግንኙንት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጉብኝት እና ዉጤቱ ፣ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ በህዳሴ ግድብ ሙሌት እና ውኃ አለቃቀቅ ላይ የተካሄደዉን ምክክር ዉጤቱን በተመለከተ ቃል- አቀባዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

 

ጌታቸዉ ተድላኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ