2008 በተፈጥሮና ጤና ረገድ | ጤና እና አካባቢ | DW | 30.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

2008 በተፈጥሮና ጤና ረገድ

2008 የጎርጎሮሳዊዉ ቀመር ለሚከተለዉ ዓለም 2009ዓ,ም ከፊቱ አድርጎ ሊሰናበት ዳርዳር እያለ ነዉ።

ከፍርስራሽ ዉስጥ የወጣችዉ ነፍሰጡር

ከፍርስራሽ ዉስጥ የወጣችዉ ነፍሰጡር

ዓመቱ መቼም ብዙ ነገር ተከናዉኖበታል፤ ሰናይ፤ አስከፊ የተፈጥሮ ክስተቶችም አልፈዉበታል። ከምንም በላይ የዓለም መሪዎችን የአየር ጠባይ በፈጣን ሁኔታ መለዋወጥና እሱን የተከሉት ጥፋቶች ሲያሳስቧቸዉ ከርመዉ ይህ ነዉ የሚባል ተጨባጭ ርምጃም ሳይወሰድ ዓመቱ ተግባሩን አከናዉኖ ለወርተረኛዉ ሊያስረክብ አንድ ቀን ቀረዉ።