20 ዓመት የሞላዉ የማንዴላ ነፃነት | ዓለም | DW | 12.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

20 ዓመት የሞላዉ የማንዴላ ነፃነት

በደቡብ አፍሪቃዉ የአፓርታይድ ስርአት ተገርስሶ፣ ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ታጋዩ የደቡብ አፍሪቃዊዉ ኔልሰን ማንዴላ ልክ የዛሬ ሃያ አመት በዛሬዋ እለት ነበር ከስር የተለቀቁት።

default

ማንዴላ ከእስራት እንደተፈቱ

ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ ሃያ አመት ልክ በዛሬዋ ቀን ከእስር ነጻ ሆነዉ Victor-Verster የተሰኘዉን እስር ቤት ለቀዉ ሲወጡ ጥቁርም ሆነ ነጭ ደቡብ አፍሪቃዊ ማዲባ፤ማዲባ እያለ ነበር በጭሁትና በሆታ የተቀበላቸዉ። ማንዴላ አንተ ነህ ይህችን አገር በፍትሃዊ መንገድ ልታራምዳት የምትችለዉ ለማለት።
ኔልሰን ማዴላ፣ የዛሬ ሃያ አመት ከቀትር በኻላ 10 ከሩብ ሲል፣ ለነጻነት ትግል 27 አመት ታስረዉ ከነበሩበት ተለቀዉ ሲወጡ ይጠብቃቸዉ የነበረዉ ከ50 ሺህ በላይ ህዝብ ማዲባ, ማዲባ እያለ ነበር በሆታ የተቀበላቸዉ። በደቡብ አፍሪቃ ነጭ እና ጥቁር ህዝብ መካከል ያለዉን ጥላቻ አስወግደህ ፍትህን ታመጣለህ በማለት። ለጥቁር ህዝቦች መብት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ከእስር ወጥተዉ በኬፕታዉን አደባባይ ባሰሙት ንግግራቸዉ በዝያን ግዜ የደቡብ አፍሪቃ ፕሪዝደንት የነበሩት ክለርክ ለዉሳኔያቸዉ እና ፍትህን በአገሪቷ ለማምጣት ላደረጉት ስራቸዉ ክብላቸዉን ገልጸዉ፣ ግን የደቡብ አፍሪቃ ህዝብ በአገሪቷ አፓርታይድ እንዲጣፋ ትግሉን ይበልጥ እንዲያጠናክር ነዉ በማለት ነበር በሃይል ቃል ህዝቡን ይበልጥ የቀሰቀሱት። አሁን ማንዴላ ከማቀቀበት እስር ቤት ወጣ ብላችሁ ትግላችሁን ብታላሉ አሉ ኔልሰን ማንዴላ በማስጠንቀቅ መጭዉ ትዉልድ እስከ መጨረሻዉ ይቅር የማይለን ከባድ ስህተት እንደሆነ እንድታዉቁት ጥቁር ህዝቦች በአገሪቷ ፍትህ ሊያገኙ ይገባቸዋል።

Fredrik Willem de Klerk Bekanntgabe Mandela Freilassung

ማንዴላን የፈቱት የቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሪዝዳንት ፍሪድሪክ ዊልያም ዲ ክሌርክ

ማንዴላ ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት እኩልነት ፍትህ የታገሉላት ደቡብ አፍሪቃ የዛሬዉ ትዉልድ በአገሪቷ የመጣለትን ነጻነት እና ፍትህ እያጣጣመ ነዉ። ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ በነጻነት የሚሰሩት መገናኛ ብዙሃን የሰራተኛ ማህበራት እንዲሁም ነጻ ህገ መንግስቷ አህጉሪቷ ዉስጥ በየትኛዉም አገር ዉስጥ ያልታየ እና በአለም ዙርያ ፍትህ ነጻነት አለ በሚባልባቸዉ የአለም አገሮች አንዳ ሆናለች። በ 1990 ዎቹ በአለም አገራት ይሰደዱ የነበሩት ከአገሪቷ ማህጸን የወጡት ምሁራን አገራቸዉ ህልዉና ፍትህ እድገትን በማየትዋ አገራቸዉን ለማገልገል ኑሮዋቸዉን በደቡብ አፍሪቃ አድርገዋል። በደቡብ አፍሪቃ በተለይ በኬፕታዉን፣ ዱርባን ጆሃንስበርግ፣ ከተሞች በኢኮነሚ የጠነከሩ በራሳቸዉ የቆሙ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃዉያን ተበራክተዋል። የተለያየ ቀለማት የቆዳ ቀለም ያላቸዉን ህዝቦችን እንና ብሄሮችን ያቀፈችዉ ደቡብ አፍሪቃ በአፓርታይዱ ስርአት ከወደቀ በኻላ በአገሪቷ እኩልነት ሰፍኖ በጭ የጎዳና ተዳዳሪ ወይም በየጎዳናዉ ላይ የሚለምን ነጭ አፍሪቃዊም ይታይ ጀምሮአል። በአፓርታይድ ስርአት ነጭ ክብር ስለ-ነበረዉ ያልታየዉን። በአገሪቷ ያሉን ነጭ ጥቁር አፍሪቃዉያን በበኩላቸዉ አፓርታይድ ከወደቀ በኻላ ለነጭ ይሰጥ የነበረዉ የትምህርት የጤና እንዲሁም የስርኣ ኮታ ቀንሶአል በማለት የአፓርታይድን መዉደቅ መወንጀላቸዉ አልቀረም። በደቡብ አፍሪቃ ጋዜጣ ተወካይ የሆነዉ ጀርመናዊ በደቡብ አፍሪቃ ሲኖር 25 አመታትን አስቆጥሮአል።
«በደቡብ አፍሪቃ ብዙሃኑ መብት የተነፈገበት፣ የሰዉ ነፍስ ርካሽ የሆነበት እና፣ ህዝብ በየቦታዉ የሚገደልበት የአስቸካይ ጉዳይ ሁኔታ ነበር የሚታየዉ ከዝያ በኻላ አፓርታይድ ተገርስሶ፣ አሁን ያለዉን ሁኔታ ስናይ ደቡብ አፍሪቃ የተሻለች አገር ሆና እናገኛታለን። አገሪቷ ዲሞክራሲን ያገኘችዉ ከብዙ ችግር እና ፈተና በኻላ ነዉ። አሁንም ቢሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች በበለጠ የተሻለ ህይወትን ማግኘት ይችላሉ»

Flash-Galerie Nelson Mandela


ጋዜጠኛዉ ይንን ሲል ዛሪ የኔልሰን ማንዴላን መፈታት ሃያኛ አመት አስመልክተን ብንደሰትም በጥንቃቄ ልናያቸዉ የሚገቡ ነገሮች አሉ ነዉ።
«አፓርታይድን ገርስሰዉ ስልጣን የያዙትን የአገሪቷን ሃይሎች በጥርጣሪ ልናያቸዉ ይገባ ይመስለኛል። ANC የተሰኘዉ በደቡብ አፍሪቃ አብላጫን ይዞ ያለዉ ፓርቲ በአገሪቷ ያለዉን ስልጣን ሁሉ ተቆጣጥሮ ነዉ የሚገኘዉ። ጉበኝነት እና አድሎ በዝያዉ በፓርቲዉ መካከል በግልጽ ይታያል፣ ሌላዉ ፓርቲዉ የዙንባቤን መንግስት ይረዳል፣ የፓርቲዉ አንዱ ትልቅ ችግር ደግሞ የኤድስ ቫይረስን ለመዋጋት ምንም አይነት ቅስቀሳን አያካሂድም። እነዚህ ጉዳዮች በኔልሰን ማንዴላ የስልጣን ዘመን የታዩ ናቸዉ፣ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አሁንም ሁኔታዉ ቀጥሎአል። አዎ የማይካድ ነዉ ባጠቃላይ አገሪቷ ላይ እድገት ታይቷል። ግን በደቡብ አፍሪቃም ብዙ አፍሪቃ አገሮች ላይ እንደሚታየዉ የአንድ ፓርቲ የበላይነት እና አስተዳደር በከፊል በማንዴላ አስተዳደር ነበር፣ ከዝያም በተተኩት በማቤኪ እንዲሁ ታይቶአል፣ አሁንም አሁንም በዙማ አስተዳደር ይሄዉ ነዉ ሁኔታ ነዉ የቀጠለዉ»
46, 664 የእስር ቤት የመለያ ቁጥራቸዉን ይዘዉ በዝያዉ በደቡብ አፍሪቃ በሮቢን ደሴት ላይ 18 አመታትን ከዝያም በኬፕታዉን አቅራብያ ባለ በአንድ ጠባብ እስር ቤት 9 አመት ባጠቃላይ 27 አመታትን በእስር ህይወታቸዉ ያሳለፉት የደቡብ አፍሪቃዊዉ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪቃ ከአርባ አመታት በላይ ቆየዉን የአፓርታይድ ስርአት በትግላቸዉ ጥለዋል። ማንዴላ እንደ የመጀመርያዉ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃዊ ፕሪዝደንት በመሆን ተመርጠዉ 1994 - 1999 አ.ም አገራቸዉን መርተዋል። በርካታ ደቡብ አፍሪቃዉያን ማንዴላ ከእስር ነጻ ሆነዉ በህይወት እናያቸዋለን ብሎ ያሰበ እንዳልነበረ ይገልጻሉ። እምደዉም ማንዴላ ከእስር ከወጡ የነጭ እና የጥቁር ህዝቦች ጦርነት በአገሪቷ ይጫራል የሚል ፍርሃትም እንደነበራችዉ ይገልጻሉ።
የ 91 አመቱ የነጻናት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ፈገግታቸዉ እና የአገራቸዉ ህዝብ ለነጻነት የሚያዜመዉን ዜማ ሲያስተጋባ እጃቸዉን ወዝወዝ እያደረጉ የሚደንሷት ዳንሳቸዉ ፈገግ ሲሉ የምትጨፈነዉ አይናቸዉ ዋነኛ ምልክታቸዉ ሆንዋል ይኸዉም በጆሃንስበር የኔልሳን ማንዴላ አደባባይ በተባለዉ ቦታ ላይ በሚገኘዉ ታዋቂ የገበያ አዳራሽ መግቢያ ላይ የኔልሰን ማንዴላን ልዩ ምልክት ፈገግታ የተላበሰዉ ከመዳብ የተሰራ ሃዉልት ለክብራቸዉ በምስጋና አቁሞላቸዋል።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ