1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

14ኛው የአፍሪቃ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2011

የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እማኛው ይግዛው ለ«DW» እንደገለጹት ዛሬ 4 ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን በ15 ኪሎ ሜትር ታዳጊ ሴቶች አንድ ኢትዮጵያዊትና አንድ ኤርትራዊት በተወዳደሩበት የብስክሌት ግልቢያ እትዮጵያ ወርቅ ስትወስድ ኤርትራ ደግሞ የብር ሜዳሊያ ወስዳለች።

https://p.dw.com/p/3F8hX
Äthiopien 14. Afrikanische Radsportmeisterschaft in Bahir Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

ኢትዮጵያ 3 ወርቆችን በማግኘት ወድድሩን በድል ጀምራለች


ዛሬ በተጀመረው 14ኛው የአፍሪቃ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ኢትዮጵያ 3 ወርቆችን በማግኘት ወድድሩን በድል ጀምራለች። የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እማኛው ይግዛው ለ«DW» እንደገለጹት ዛሬ 4 ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን በ15 ኪሎ ሜትር ታዳጊ ሴቶች አንድ ኢትዮጵያዊትና አንድ ኤርትራዊት በተወዳደሩበት የብስክሌት ግልቢያ እትዮጵያ ወርቅ ስትወስድ ኤርትራ ደግሞ የብር ሜዳሊያ ወስዳለች። በ30 ኪሎ ሜትር ታዳጊ ዎንዶች ኢትዮጵያ ወርቅ፣ ኤርትራ ብር፣ሩዋንዳ ደግሞ የነሀስ አሸናፊ ሆነዋል። ከ23 ዓመት እደሜ በታች ሴቶች ኢትዮጵያ ወርቅ፣ ኤርትራ ብር፣ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ የነሃስ ወስዳለች። ከ23 ዓመት እደሜ በታች ወንዶች ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ ወርቅ፣ሩዋንዳ ብር፣ ኢትዮጵያ የነሀስ ማሸነፏን አቶ እማኘው ተናግረዋል። ውድድሩ ነገም በሌሎች ርቀቶች እንደሚቀጥል ኃላፊው አመልክተዋል። 


ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ