148 የጋህነን አባላት እጃቸውን ሰጡ | ኢትዮጵያ | DW | 22.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

148 የጋህነን አባላት እጃቸውን ሰጡ

የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በምህጻሩ ጋህነን አመራር እና አባላት መሆናቸዉ የተገለፀ 148 ሰዎች እጃቸዉን ለመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መስጠታቸዉ ተገለጸ። የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ ቱት ዛሬ ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት ለሦስት ወራት ከተካሄደ ድርድር በኋላ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:46

148 የጋህነን አባላት እጃቸውን ሰጡ

የጋምቤላ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ጋህነን)ቁጥር ሁለት በመባል የሚጠራው ቡድን አባላት ሰሞኑን ለኢትዮጵያ መንግሥት እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሀገራቸዉ መመለሳቸው ተሰምቷል። ይህ የሆነውም ከቡድኑ ጋር በተደረሰ ስምምነት ነው። እጃቸውን ከሰጡት 148 የጋህነን ቁጥር ሁለት አመራር እና አባላት መካከል ከ 18 በላዩ ሴቶች እንደሆኑ የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ ቱት ዛሬ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። እንቅስቃሴውን በተመለከተ ሲያስረዱም  « እነዚህ ሰዎች ኤርትራ ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።  ወደ ደቡብ ሱዳንም የገቡበት ሁኔታ ነበር። » ብለዋል።

Karte Äthiopien Südsudan Gambella Englisch

የጋምቤላ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አባላት በደቡብ ሱዳን እና በኤርትሪያ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር

ሺንዋ ዜና ምንጭ አማፂያን እንደሆኑ የጠቆማቸው እነዚህ ወገኖች በትክክል እነማን ናቸው? አላማቸውስ ምን ነበር? እንደ አቶ ጋትሉዋክ ገለፃ « ጋህነን ቁጥር ሁለት በተለይ ኤርትራ ውስጥ የተለያዩ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው። ጋህነን ቁጥር ሁለት የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ነው።»

በተለያየ አካባቢ የነበሩትን የዚሁ የጋህነን ቁጥር ሁለት እንቅስቃሴ አባላትን ለማግባባት ጊዜ እንደወሰደ እና ከሦስት ወራት በኋላ ሰላም ፈጣሪ ስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ጋትሉዋክ ተናግረዋል። « መንግሥታችን በሰላማዊ መንገድ ከእነሱ ጋር ከስምምነት እንዲደርሱ አድርጓል። አላማው  የሀገራችንን እና የክልላችንን ሰላም ለመጠበቅ ነው። እጃቸውን የሰጡት አባላትም ከጥር 11 ጀምሮ የተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ እንደሆነ እና ከስልጠናው በኋላ ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው እንደሚቀላቀሉ ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ አክለው ገልጸዋል።  

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ
 

Audios and videos on the topic