125 ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረው የካርል ዛይስ ድርጅት | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 30.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

125 ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረው የካርል ዛይስ ድርጅት

በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ፤ የኢንዱስትሪው አብዮት በእንግሊዝ ሀገር ከተጀመረ በኋላ ፣ በአፋጣኝ የዚህ እንቅሥቃሤ ተጋሪና አራማጅ ለመሆን ከበቁት ጥቂት ግንባር ቀደም ሃገራት መካከል አንዷ ጀርመን መሆኗ የሚታበል አይደለም። የፈላስፎችና የተመራማሪዎች

default

ሀገር ትሰኝ የነበረችው ሀገር ፣ ሳይንሳዊ ዕውቀትን ፣ ሥነ ቴክኒክን ለሕብረተሰብ ጠቀሜታ እንዲውል በየረድፉ ባደረገችው ምርምር በተለይ ከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ገደማ አንስቶ እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፤ ከዚያ ወዲህም ቢሆን፤ ለአያሌ ግኝቶች መሠረት ለመሆን መብቃቷ እሙን ነው። አገሪቱ ለሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ምርምር ላቅ ያለ ግምት ከመስጠት የቦዘነችበት ጊዜ የለም።

BdT 80 Jahre Jenaer Planetarium Laserprojektion

ጀርመን ውስጥ ከድሮ ጀምሮ ፣ ከታወቁት ሳይንስንና ሥነ ቴክኒክን መሠረት አድርገው ከተቋቋሙት ድርጅቶች ወይም ኩባንያዎች መካከል፤ የዓይን መነጽር፤ ካሜራ ፤ ኢምንት ነገሮችን አጉልቶ የሚያሳይ መነጽር(ማይክሮስኮፕ)፤እጅግ ራቅ ብለው በኅዋ የሚገኙ የሰማይ አካላትን አቅርቦ የሚያሳይ ቴሌስኮፕ፣ለቀዶ ህክምናና ለመሳሰለው የሚጠቅሙ የረቀቁ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ሠርቶ በማቅረብ እጅግ የታወቀው ካርል ዛይስ ነው። ድርጅቱ በመሥራቹ ስም ነው የሚጠራው።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic