የኦሮሚያ ርዕሠ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበዓሉ ላይ ለታመደዉ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠር ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ አስቸገሪ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ፣ ይሁንና አሁንም ጀግና ትዉልድ ስላላት አትፈርስም ብለዋል
የኢትዮጵያ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት በየአደባባዩ የፍቅር፣የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና የአንድነትን አስፈላጊነት የተናገሩበትን 125ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ እንኳ በአንድነት አላከበሩትም።ከቀዳሚዉ ዘገባችን እንደተከታተላችሁት ብሔራዊዉ በዓል አዲስ አበባ አፄ ምኒሊክ መታሰቢያ አደባባይ ሲከበር፣ የኦሮሚያ መስተዳድር ደግሞ በዓሉን እዚያዉ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አክብሯል።የኦሮሚያ ርዕሠ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበዓሉ ላይ ለታመደዉ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠር ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ አስቸገሪ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ፣ ይሁንና አሁንም ጀግና ትዉልድ ስላላት አትፈርስም ብለዋል።ታሪክም በሽለላና በፌስ ቡክ ጨዋታ አይሰራም-እንደ ርዕሠ መስተዳድሩ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ