1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

125ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ ብሔራዊ በዓል

ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2013

አዲስ አበባ ምኒሊክ አደባባይ በተከበረዉ በዓል ላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣የከተማይቱና የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳሕለወርቅ ዘዉዴ ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል መንፈስ ከኢትዮጵያዉያን አልፎ ለሰዉ ልጅ በሙሉ የሕይወት መመሪያ ነዉ ብለዋል

https://p.dw.com/p/3q6Rt
Äthiopien Adwa  125. Unabhängigkeitstag
ምስል Solomon Muchie/DW

125ኛዉ የአድዋ ድል በዓል አንድነት፣ ትብብርና የሐገር ፍቅር ተሰብኮበታል

የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ወራሪ ጦርን አድዋ ላይ ድል ያደረጉበት 125ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ዛሬ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በደማቅ ሥርዓት ተከብሮ ዉሏል።አዲስ አበባ ምኒሊክ አደባባይ በተከበረዉ በዓል ላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣የከተማይቱና የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳሕለወርቅ ዘዉዴ ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል መንፈስ ከኢትዮጵያዉያን አልፎ ለሰዉ ልጅ በሙሉ የሕይወት መመሪያ ነዉ ብለዋል።የባሕልና ቱርዚም ሚንስትር ኂሩት ካሳዉ እንዳሉት ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ከአድዋ ጀግኖች፣ ፍቅርን፣ መተማመንና በጋራ መቆን መማር አለባቸዉ።በንግግራቸዉ ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባነት ይልቅ የመላዉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን መሆናቸዉን ያንፀባረቁት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዓሉ የሚከበረዉ ለኢትዮጵያዉያን «ተግዳሮት» ያሉት ፈተና በበዛበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ