12 ተማሪዎች (IS)ን ለመቀላቀል ከሱዳን ወጡ | አፍሪቃ | DW | 28.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

12 ተማሪዎች (IS)ን ለመቀላቀል ከሱዳን ወጡ

በሱዳን የህክምና እና ስነ-ቴክኒክ የግል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተመዘገቡ 12 ተማሪዎች እራሱን «እስላማዊ መንግስት» እያለ የሚጠራውን ቡድን ለመቀላቀል ከካርቱም ወደ ቱርክ ማቅናታቸው ተዘገበ። ከተማሪዎቹ መካከል አብዛኞቹ የውጭ ሀገር ዜግነት እንዳላቸው የዩኒቨርሪቲው ዲን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

ከሦስት ወራት በፊትም ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ የብሪታንያ ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ሱዳናውያን ተማሪዎች በቱርክ አሳብረው ወደ ሶሪያ ሳይሻገሩ አልቀረም ተብሏል። የካርቱም አየር ማረፊያ ባለሥልጣናት ተማሪዎቹ ወደ ቱርክ ስለመጓዛቸው ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የተማሪዎቹ ቤተሰቦች በበኩላቸው ካለፈው ዓርብ አንስቶ ተማሪ ልጆቻቸውን እንዳላዩ መናገራቸውን የዩኒቨርሲቲው ዲን ዶክተር አህመድ ባቢኪር አስታውቀዋል። መጥፋታቸው ከተነገረላቸው ሰባቱ ተማሪዎች መካከል አንድ ብሪታንያዊ፣ ሁለት ካናዳውያን፣ አንድ አሜሪካዊ እና ሁለት ሱዳናውያን ይገኙበታል ተብሏል። ከ12 ተማሪዎች መካከል ሦስቱ ሴቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ