1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

12 ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር እና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 12 2001

በርሊን ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው አስራ ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ ትናንት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ በወንዶች አስር ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አግኝታለች ።

https://p.dw.com/p/JDh2
ቀነኒሳ በቀለምስል AP Photo/Mark Baker

ትናንት ምሽት ልማደኛው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የአስር ሺህ ሜትሩን ውድድር በ26 ደቂቃ 46.31 ሰከንድ በአንደኝነት ጨርሷል ። ቀነኒሳ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በ 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ሲያሸንፍ የትናንቱ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ። እ.ጎ.አ በ 2003 ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ ፣ በ2005 ሄልሲንኪ ፊንላንድ እንዲሁም በ2007 ኦሳካ ጃፓን የተካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና የ 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች አሸናፊ ቀነኒሳ በቀለ ትናንትም ለአራተኛ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የወርቁን ሜዳልያ አጥልቋል ። ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ደግሞ ሁለተኛ ወጥቷል ። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የቀነኒሳን ድል መነሻ አድርጎ በኢትዮጵያ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ላይ ያተኮረ ዘገባ አጠናቅሯል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ