118 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል አከባበር | ኢትዮጵያ | DW | 02.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

118 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል አከባበር

118 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል መታሰብያ በኢትዮጵያና በተለያዩ የዓለም ሃገራት በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት ተከበረ።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፤ አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘዉ የአፄ ሚኒሊክ አደባባይ የጥንታዊ ኢትዮጵያ የአርበኞች አባላት፣ የመንግሥት ተወካዮች እና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል። የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ዶክትር ታቦር ገመድህን፤ በአፄ ሚኒሊክ ሃዉልት ስር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። ኢትዮጵያዉያን የጣልያን ወራሪ ጦርን ድል ያደረጉበት ይህ በዓል፤ ለአፍሪቃዉያን እና ለመላዉ ጥቁር ሕዝብ ደግሞ ኩራትን ማቀዳጀቱ ይታወቃል። በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ የአፍሪቃ አገሮች ላደረጉት ከፍተኛ የነፃንት ተጋድሎ የኢትዮጵያዉያኑን፤ የአድዋ ድል በቀደምትነት የሚጠቅሱበት እና የህሊና ጥንካሬን የሚያገኙበትም ነበር።

የ118 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ በተለይ አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘዉ የአፄ ሚኒሊክ አደባባይ እንዴት ተከብሮ እንደዋለ ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሎ የድምፅ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic