1085 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ | ኢትዮጵያ | DW | 21.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

1085 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም፣ ባለፉት 3 ቀናት 1085 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ሀገራቸው መግባታቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ሳዑዲ አረብያ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀረበላት ጥያቄ መሠረት ከእስር የፈታቻቸው ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም፣ ባለፉት 3 ቀናት 1085 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ሀገራቸው መግባታቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያኑ የመጓጓዣ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደየቤተሰቦቻቸው እንደተሸኙም ተገልጿል። ቃል አቀባዩን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኳል። 


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic