108ኛው ፓርቲ ተመሠረተ  | ኢትዮጵያ | DW | 26.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

108ኛው ፓርቲ ተመሠረተ 

በኢትዮጵያ 108 ኛ ሆኖ የተመሠረተው ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ  ተንሰራፍቶ የቆየውን አግላይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከስረ መሠረቱ ለማስወገድ እሠራለሁ አለ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

«የፓለቲካ አቅጣጫ ወግ አጥባቂ ለዘብተኛ መሆኑን ገልጿል»

 የሚከተለው የፓለቲካ አቅጣጫ ወግ አጥባቂ ለዘብተኛ መሆኑን ያመለከተው አዲሱ ፓርቲ እስካሁን ያልተፈቱ ውስብስብ ችግሮችን አካታች እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በጋራ እንዲፈቱ እንደሚሠራም አስታውቋል። በአሁኑ ሰአት መንግሥት ከብዛት ይልቅ ሰብሰብ ብላችሁ ጠንካራ ፓርቲ በማዋቀር ተንቀሳቀሱ በሚልበት ወቅት ተጨማሪ የመመስረቱን ተገቢነት የተጠየቀው ፓርቲ፣  የመደራጀት መብትን መንግሥት እስካልገደበ ድረስ ችግር እንደሌለው ነው የገለጸው። በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነቶች ምሁር የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦችንና አመለካከቶችን ማሰባሰብ ቢኖርባቸውም ከዚህ በተቃራኒ መሆናቸውን፤ ይህም የተቋማት ግንባታ እና የመሪዎች ሰብእና አለመጠናከር ነጸብራቅ መሆኑን አመልክተዋል። ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን ልኮልናል።  

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች