1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖለቲካ በፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን

ማክሰኞ፣ ሰኔ 11 2016

በአውሮጳ የሰሞኑ የምክር ቤት ምርጫ ውጤት በፈረንሳይ ፖለቲከኞችን ብቻ አይደለም ያመሰው ። ጉዳዩ በፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ውስጥም ገብቷል ። ምክንያቱ ምን ይሆን?

https://p.dw.com/p/4hD5K
Euro 2024 Österreich - Frankreich
ምስል Andreea Alexandru/AP Photo/picture alliance

በአውሮጳ የሰሞኑ የምክር ቤት ምርጫ ውጤት በፈረንሳይ ፖለቲከኞችን ብቻ አይደለም ያመሰው ። ጉዳዩ በፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ውስጥም ገብቷል ። በተለይ አፍሪቃዊ ዝርያ ያላቸው ታዋቂ ተጨዋቾች ቀኝ አክራሪ ዘረኞች ወደ ሥልጣኑ እንዳይመጡ ሲሉ ፖለቲካዊ ንግግር በማሰማት በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ጀምረዋል ።

የፈረንሣይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን  በአውሮጳ እግር ኳስ የምድብ ግጥሚያ  ሰኞ፤ ሰኔ ቀን፣ 2016 ዓም ምሽት ከኦስትሪያ ጋ ተጋጥሞ እንደምንም 1 ለ0 አሸንፏል ። በእለቱ አምበሉ ኬሊያን እምባፔ አፍንጫው ላይ በደረሰበት ጉዳት ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል ። እነ ኬሊያን እምባፔ እንዲሁም ማርኩስ ቱራምን ጨምሮ ጸረ ቀኝ አክራሪ ንግግር እያሰሙ ነው ። ለመሆኑ የፖለቲካ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት ወደ ፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ ሊገባ ቻለ? ከቃለ መጠይቁ ሙሉውን ይከታተሉ ። 

ሐይማኖት ጥሩነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ