ፕሬዝደንት ኦባማ የብራስልስ ጉብኝትና ጉባኤ | ዓለም | DW | 26.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ፕሬዝደንት ኦባማ የብራስልስ ጉብኝትና ጉባኤ

ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ሩስያን በመቃወም የያዙትን የተባበረ አቋም ዳግም ገለፁ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማና የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኽርማን ቫን ሮምፖይ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆሴ ማኑዌል ባሮሶ ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ዛሬ ከተነጋገሩ በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ ሁለቱ ወገኖች ነፃ የንግድ ቀጠና ለመመሥረት ከስምምነት እንደሚደርሱም አስታወቁ ። ኦባማ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ዩናይትድ ስቴትስና አውሮፓ በሩስያ ላይ የሚጥሉት የኤኮኖሚ ማዕቀቦች ቅንጅት እጅግ በጣም ጥሩ ነው ሲሉ አወድሰዋል ። ሩስያ በጀመረችው መንገድ መጓዟን ከቀጠለች ይበልጥ እንደምትገለልም አስጠንቅቀዋል ። በኦባማ እምነት የሩስያ ማስፈራሪያም የድክመቷ ማሳያ መሆኑን አስታውቀዋል ።
« ሩስያ አንዳንድ የቅርብ ጎረቤቶቿን የምታስፈራራ የአካባቢው ኃያል መንግሥት ናት ። ይህን የምታደርግው ግን ጠንካራ ስለሆነች አይደለም በድክመቷ ምክንያት እንጂ ።»


ኽርማን ቫን ሮምፖይ በበኩላቸው ሩስያ በክሪምያ የወሰደችው እርምጃ በ21 ኛው ዘመን የተፈፀመ አሳፋሪ ድርጊት ነው ብለውታል ። ክሪምያ የሩስያ አካል መሆኗንና ሩስያም ግዛቲቱን በፌደሬሽኗ ማጠቃለሏን እውቅና እንደማይሰጡ ተናግረዋል ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በአዉሮጳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ቀጥሎ ዛሬ ብራስል ቤልጅግ ይገኛሉ። በብራስልስ ከአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ጋ ካደረጉት ዉይይት በኋላም ከሰዓት በኋላ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሁለቱ ወገኖች የጋራ ዉይይት የኤኮኖሚ ግንኙነታቸዉን ማጠንከርን ቢጨምርም ትልቁ መነጋገሪያቸዉ የነበረዉ የዩክሬን ጉዳይ ነዉ። በዚህ ወቅትም ኦባማ የአዉሮጳ ኅብረትና የአሜሪካን ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማመልከት፤ በተለይ የሰሞኑ አቢይ ዜና የሆነዉ የዩክሬን ሩሲያ ዉዝግብን በሚመለከት ሁለቱ ወገኖች አቋማቸዉ አንድ መሆኑን ገልጸዋል። የጋዜጣዊ መግለጫዉን የተከታተለዉ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤን በወቅቱ የተነሱ ነጥቦችን እንዲያጋራን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋeu መሐመድ

Audios and videos on the topic