ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ በይፋ ስልጣን ለቀቁ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ በይፋ ስልጣን ለቀቁ

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ ከአምስት ዓመት ሥልጣን በኋላ ዛሬ በወታደራዊ ስነ ስርዓት በበርሊኑ የ«ቤሊቪዉ» ቤተ መንግሥት በይፋ ተሸኙ። ወታደራዊ ስነ ስርዓቱ የጀርመን ጦር ከሚያዘጋጃቸው ስነ ስርዓቶች ከፍተኛው ነው።

በዝግጅቱ ላይ በሃገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በነፃ በጎ አገልግሎት የሚሰጡ 300 ሰዎችን ጨምሮ ባጠቃላይ 600 እንግዶች እንደተገኙ ታዉቋል። ጋዉክ ከዚህ ቀደም በተደረገላቸዉ ቃለ ምልልስ ከእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል። 
« ሥልጣኔን ብለቅም የእያንዳንዱ ኅብረተሰብ አካል ሆኜ ከፖለቲከኞች ጎን ይህ የኛ ዴሞክራሴ ነዉ ይህ የኛ ነፃነት ነዉ ብዬ እናገራሉ።»  
የ 77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ በእድሜያቸው ምክንያት ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን እንደማይወዳደሩ አሳውቀው ነዉ ስልጣኑን የሚለቁት።  ጋውክን የሚተኩት የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ባለፈዉ እሁድ በይፋ ስልጣኑን ተረክበዋል።     

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ