ፕሬዚዳንት ቡተፍሊካ ከስልጣን እንዲወርዱ ተጠየቀ | አፍሪቃ | DW | 27.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ፕሬዚዳንት ቡተፍሊካ ከስልጣን እንዲወርዱ ተጠየቀ

እድሜም ጤናም የከዳቸዉ የ82 ዓመቱ ፖለቲከኛ ቡተፈሊካ የተሽከርካሪ ወንበር ቁራኛ ናቸዉ።ሕዝባቸዉም ከከዳቸዉ ቆይተዋል። ታማኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጄኔራላቸዉ ተደገሙ። ጄኔራሉ እንዳሉት የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥት በሚደነግግዉ መሠረት የሕግ-መወሰኛዉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የፕሬዝደንትነቱን ሥልጣን ተረክበዉ ሐገሪቱን ለ45 ቀናት መምራት አለባቸዉ።

የአልጀርያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አሕመድ ኡያሂአ፤ ፕሬዚዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ ከስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ። በተሽከርካሪ ወንበር የሚንቀሳቀሱት የ 82 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ቡተፍሊካ ለሽግግሩ ሂደት መንገዱን ክፍት ማድረግ አለባቸዉ ሲሉ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንዲለቁ የጠየቁበትን ምክንያት ተናግረዋል። የአልጀርያ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ጋኤድ ሳላሕ ትናንት የሐገሪቱ ፕሬዝደንት አብዱል አዚዝ ቡተፈሊቃ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዉ ከሳምንታት በፊት ጀምሮ ነበር። ፖለቲካዊ ቀዉስ ዉስጥ የምትገኘዉ በቆዳ ስፋትዋ ከአፍሪቃ ትልቅ በሆነችዉ በአልጀርያ በጤና ችግር ላይ የሚገኙት አዛዉንቱ ፕሬዚዳንት አብደልአዚዝ  ቡተፍሊካ ከስልጣን እንዲለቁ ከፍተኛ ተቃዉሞ ሲደረግ ነበር የሰነበተዉ። የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸዉ በሃገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት ግልበጣ እየተካሄደ ነዉ ሲሉ ስጋታቸዉን እየገለፁ ነዉ። 

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ