የቀድሞ ዮጎዝላቪያን የሚመለከተው የተባበሩት መንግስታት ልዩ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔ አሳለፈ። የሠርቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሚሉቲኖቪች፤ በኮሶቮ በተከሰተው የጦር ወንጀለኝነት ጥፋት ከቀረበባቸው ክስ በነፃ ተሰናብተዋል። ውሳኔውን ይፋ ያደረገውም በኔዘርላንድ ሄግ ያስዋለው ችሎት ነው። ሌሎች አምስት ተከሳሾች ከአስራ አምስት እስከ ሀያ ሁለት ዓመታት የሚደርስ የእስራት ቅጣት እንደተበየነባቸው ታውቓል።