ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሴኔጋል | አፍሪቃ | DW | 27.02.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሴኔጋል

በምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር -ሴኔጋል፤ እጅግ አከራካሪ ሆኖ የተገኘው የአገሪቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ትናንት ተካሂዷል። በምርጫው 60 ከመቶ የሚሆነው ድምጽ መስጠት የሚፈቀድለት ዜጋ መካፈሉን አዣንስ ፕረስ የዜና ወኪል ገለፀ።

በምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር -ሴኔጋል፤ እጅግ አከራካሪ ሆኖ የተገኘው የአገሪቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ትናንት ተካሂዷል። በምርጫው 60 ከመቶ የሚሆነው ድምጽ መስጠት የሚፈቀድለት ዜጋ መካፈሉን አዣንስ ፕረስ የዜና ወኪል ገለፀ። እንዲሁም የአገሪቱ የምርጫ ኮሚቴ ኃላፊ ስለምርጫው ሲናገሩ፤ ምንም እንኳን ከምርጫው በፊት በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍሎት ተደጋግሚ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ቢካሄድም ምርጫዉ ግን በአጠቃላይ የዕለቱ ዕለት በሰላማዊ መልኩ ተፈፅሟል።

የ 85 ዓመቱ አንጋፋ ፕሬዚደንት -አብዱላዬ ዋድ- ለሶሥተኛ ጊዜ ከ13 የተቃውሞ ወገን ተወካዮች ጋር እጩ ተፎካካሪ ሆነው ትናንት ለምርጫ ቀርበዋል። የዋድ በዚህ ምርጫ መካፈል መፈለግ ባለፉት ወራት የአገሪቱን ሰላም ሲያናውጽ ቆይቷል። ዋድ እንደገና ለመፎካከር የተነሱት የፕሬዚደንቱን ሥልጣን በሁለት የአስተዳደር ዘመን የሚገድበው የአገሪቱ ሕግ ገሃድ ከመሆኑ በፊት ሥልጣን ላይ መውጣታቸውን በመጥቀስ እኔን አይመለከትም በሚል ነው።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 27.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14AuY
 • ቀን 27.02.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14AuY