ፕሪዚዳንት ኬኒያታና የተራዘመዉ የICC የፍርድ ሂደት | ዓለም | DW | 24.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ፕሪዚዳንት ኬኒያታና የተራዘመዉ የICC የፍርድ ሂደት

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ICC በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል የተከሰሱት የኬንያዉ ፕሬዝዳት ኡሁሩ ኬንያታን ለመመልከት የያዘዉን ቀጠሮ አራዘመ። ፍርድ ቤቱ ቀጠሮዉን ያዘወረዉ፤ አቃቤ ሕግ የፍርድ ሂደቱ በሌላ ቀን እንዲጀመር በመጠየቁ ነበር።

ኬንያ ዉስጥ እንደ ጎ,አ 2007 ማብቂያ ከተደረገዉ ምርጫ በኋላ በተቀሰቀሰዉ ግጭት የተገደሉ ሰዎች ቤተሰቦች ግን በአስቸኳይ ካሳ ማግኘትን እንደሚፈልጉ በመግለፅ ላይ ናቸዉ።

Logo des Internationalen Strafgerichtshof in Den Haag

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ትናንት ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በኬንያዉ ፕሬዝዳት ኡሁሩ ኬንያታ ላይ የተመሰረተዉን ክስ ለመስማት የካቲት አምስት ይዞት የነበረዉን ቀነ ቀጠሮ ለሌላ ግዜ ተዛዉሮአል። ይህ የታወቀዉ አቃቤ ህጉ የፍርዱ ሂደት እንዲዛወርለት ከጠየቀ በኃላ መሆኑ ተመልክቶአል። የኬንያዉ ፕሬዝዳት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትላቸዉ ዊልያም ሩቶ፣ በ 2000 ዓ ም በሀገሪቱ ምርጫ በተካሄደ ማግሥት የተፈጠረውን ሁከትና ግድያ በማቀነባበር በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት ክስ እንደመሰረተባቸዉ ይታወቃል። ዘ ሄግ ፤ኔዘርላንድ የሚገኘዉ ዓለማቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ክስ የሚጀመርበት ቀን መዛወሩን ይፋ ካደረገ በኋላ በኬንያ ስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የሚገኙ የድህረ ምርጫ ኽዉከት ሰለቦችና ቤተሰቦቻቸዉ ዋና ተጠሪ ፓትሪክ ሙቸሪ እንዳሉት፤ በዚም አለ በዛ ካሳ ለጉዳተኞች መከፈል አለበት፤

«ኬንያዉያን ICC ባሳለፈዉ ዉሳኔ ደስተኞች አይደለንም። ምክያቱም ከዚህ ምንም አይነት መፍትሄ አናገኝምና ነዉ። ስለዚህ ICC ን የምንጠይቀዉ የፍርድ ሂደቱን እንዲቀጥል እና ጉዳዩ መቋጫ ሲያገኝ መንግስትም ሆነ ማንኛዉም አካል፤ በኬንያ ይህ ወንጀል ለተፈፀመበት ካሳ እንዲሰጥ ነዉ»


ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በፕሪዚዳንት ኬንያታና በምክትላቸዉ ላይ የመሰረትነዉን ክስ በመቃወም፤ በርካታ አፍሪቃዉያን ሀገራት ተቃዉሞአቸዉን በማሰማት ከፍርድ ቤቱ አባልነት ለመዉጣት እስከ መዉጣት ዉሳኔ ላይ ደርሰዋል።
ኬንያዉያንም ቢሆኑ ፣ አንድ ወቅት የፍርድ ቤቱን እርምጃ ይደግፉ እንደነበረ ቢታወቅም፤ የኬንያ ፓርላማው በአብላጫ ድምጽ ፤ ሃገሪቱ ከ ICC እንድትወጣ መወሰኑ የሚታወስ ነው። በያኔው የኬንያ ድህረ ምርጫ ማግሥት ለሳምንታት በተካሄደው የጎሣዎች ግጭት ከ 1,000 በላይ ኬንያውያን መገደላቸውና 600,000 ከቀየአቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic