ፔተር ሊምቡርግ የወደፊቱ የዶይቸቬለ አስተዳዳሪ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 17.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ፔተር ሊምቡርግ የወደፊቱ የዶይቸቬለ አስተዳዳሪ

ፔተር ሊምቡርግ የወደፊቱ የዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ዛሬ ተመረጡ ። የዶይቸ ቬለ የመገናኛ ብዙሃን ስርጭት ቦርድ ሊቀመንበር ቫለንቲን ሽሚት ሊምቡርግ መመረጣቸውን በርሊን ውስጥ ከተካሄደ ስብሰባ በኋላ አስታውቀዋል ።

የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያ ፣ የፕሮዚብን ዛት አይንስ የኢንፎርሜሽን ክፍል ሃላፊ ሊምቡርግ ፣ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ በአብላጫ ድምፅ ነው የተመረጡት ። ከ17ቱ የቦርዱ አባላት 14 ቱ የድጋፍ ድምፅ ሲሰጧቸው አንድ የተቃውሞ ና 2 ድምፀ ተዐቅቦም ነበር ።
ፔተር ሊምቡርግ ፣ እ ጎ አ መስከረም 30 2013 የሥልጣን ዘመናቸው የሚያከትመውን የ68 አመቱን ኤሪክ ቤተርማንን ተክተው ያገለግላሉ ። ቤተርማን፤ እ ጎ አ ከ 2001 ዓ ም አንስቶ ዶይቸ ቬለን ያስተዳደሩና ፤ ድርጅቱ አዳዲስ አገልግሎቶችን እንዲያቀርብ በመቀየስ ጭምር የሚታወሱ ስራ አስኪያጅ ናቸው ።

Erik Bettermann, Intendant der Deutschen Welle

ኤሪክ ቤተርማን ለ12 አመታት በዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል።

« ዶይቸ ቬለ የጀመረውን አዳዲስ አገልግሎቶች የበለጠ አጠናክሮ የጀርመንን የአለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረት እንዲያሻሽል ፔተር ሊምቡርግ የሚጠበቅባቸውን በሙሉ የሚያሟሉ ጋዜጠኛ ናቸው» ሲሉ፤ ሽሚት ተናግረዋል።

በተለያዩ ቋንቋዎች የዶቼቬለን የመገናና ብዙሃን አገልግሎት ማስፋፋት

የ 52 አመቱ ሊምቡርግ የዶቹቬለ የመገናኛ ብዙሃን ስርጭት ቦርድ በርሳቸው ላይ ፅኑ እምነት በመጣሉ አመስግነዋል ። « በሚመጡት አመታት አገራችን በአለም ውስጥ ያላትን ተቀባይነት ለማጎልበት ካለው ተግዳሮት አንፃር ባለኝ አቅም ሁሉ የሚቻለኝን አደርጋለሁ ። ከወጣትነቴ አንስቶ ከጀርመን ውጭ ባሳለፍኳቸው ጊዜያት የዶይቸ ቬለ ዝግጅቶች ጠቃሚ የህይወት ተሞክሮዮ አካል ነበሩ ። ከባልደረቦቼ ጋር የዶቼቬለን የጋዜጠኝነት በጎ ስም በመጠበቅ ፣ የራድዮ ጣቢያውን የተለያዩ ቋንቋዎችና የተለያዩ የመገናና ብዙሃን አገልግሎቶች ይበልጥ ማዳበር እፈልጋለሁ። ሌላው ግቤ ዶቼቬለ እንደ ARD እና ZDF ካሉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ከሚሰጡ ከሌሎች የጀርመን ጣቢያዎች ጋ ትብብሩን ይበልጥ ማጠናከር ነው ። »
ፔተር ሊምቡርግ የብሔራዊ ወታደራዊ አገልግሎት ካጠናቀቁ በኋላ በቦን ከተማ የህግ ትምህርት አጥንተዋል ። እ ጎ አ 1987 ዓ ም የመጀመሪያውን የህግ ብሔራዊ ፈተና ወሰዱ። ከዚያም እጎአ ከ1988 እስከ 1989 በጀርመን የቴሌቪዥን ጣቢያ (DFA) በቦን እና በለንደን ከተማ የጋዜጠኝነት ስልጠና ወስደዋል ።
በቀድሞዋ የምስራቅ ጀርመን ከተማ ላይፕዚግ በዘጋቢነት የሰሩት ሊምቡርግ እጎአ ከ1990 ጀምሮ የአውሮፓ እና የኔቶ ቃል አቀባይ በመሆን ለጀርመን ዲ-ኤፍ-ኤ እና ዛት-አይንስ ጣቢያዎች ከብራስልስ ይዘግቡም ነበር ። እጎአ በ1996 የፕሮዚብን ጣቢያን ሃላፊነት ተረከቡ ። በ 1999 የ N24 ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና አዘጋጅነት እና በፕሮዚብን ጣቢያ የፖለቲካ ክፍል ኃላፊነት ማገልገል ጀመሩ።

Deutsche Welle Bonn Funkhaus Gebäude Schürmann Bau Foto DW/Per Henriksen 04.09.2012. # DW2_6035.

የዶይቸ ቬለ የቦን መቀመጫ

እጎአ 2004/05 እና 2008/09 ከበርሊን በሚሰራጨው ፑል-በተባለው የግል ቴሌቬዥን ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅነት ፣ ከ2008-2010 ደግሞ ተመልሰው በ N24 ጣቢያ በዋና አዘጋጅነት አገልግለዋል ። ከ 2008 አም አንስቶ የዛት አይንስ ቴሌቪዥን ዜና አቅራቢ፣ ከ2010 ዓም አንስቶ ደግሞ የፕሮ ዚብን ዛት አይንስ ነባር ምክትል ፕሬዝዳንትም ነበሩ ። ሊምቡርግ የጀርመን ፌደራላዊ ምክር ቤት የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት ዳኞች ሊቀመንበር፣ አክስል ሽፕሪንገር አሳታሚ ድርጅት -ለወጣት ጋዜጠኞች የሚሰጠው ሽልማት ዳኞች ቡድን አባል፣ የጀርመን የጳጳሳት ጉባዔ አሳታሚ ኮሚሽን አማካሪ እና የካቶሊካዊያን የግብረ ሰናይ ድርጅት የ« ማልቴዘር »አባልም በመሆን አገልግለዋል። ቦን ከተማ የተወለዱት ሊምቡርግ ፣ ያደጉት ሮም ፣ፓሪስ አቴንስና ብራስልስ ነው ። ሊምቡርግ ባለትዳር እና የ ሶስት ልጆች አባት ናቸው።

ዮሀንስ ሆፍማን

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

ቪድዮውን ይመልከቱ። 01:14
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
01:14 ደቂቃ

ፔተር ሊምቡርግ የወደፊቱ የዶይቸቬለ አስተዳዳሪ


Audios and videos on the topic