ፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያዉያቱ አትሌቶች ድል | ስፖርት | DW | 05.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያዉያቱ አትሌቶች ድል

ፈረንሳይ ፓሪስ ውስጥ በተደረገ የዳያመንድ ሊግ የአትሌቲክስ ፍልሚያ ገንዘቤ ዲባባ ድል ቀናት።

ገንዘቤ ዲባባ የ5000 ሜትሩን የሩጫ ውድድር ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 14:15.41 እንደሆነ ተጠቅሷል። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አልማዝ አያና ገንዘቤን በመከተል 14:21.97 ላይ በመግባት ሁለተኛ ሆናለች። ኬንያውያን ሶስተኛ እና አራተኛ ሲወጡ ሰንበሬ ተፈሪ እና ገለቴ ቡርቃ አራተኛ እና አምስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።
አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን እንደሚሰበርበት ተጠብቆ የነበረዉ የኢትዮጵያዉያኑ አትሌቶች የአትሌት ገንዘቤ ዲባባና አልማዝ አያና የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ፉክክር ለጥቂት አዲስ የዓለም ክብረወሰንን ሳያስመዘግብ ቢያልፍም በዉድድሩ አዲስ ሰዓት በማስመዝገብ መጠናቀቁን የፓሪስዋ ወኪላችን በላከችልን ዘገባ አመልክታናለች።

ሐይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic