ፓሪስ፤ የአየር ንብረት ጉባዔ ተቃውሞ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 29.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ፓሪስ፤ የአየር ንብረት ጉባዔ ተቃውሞ

በፈረንሳይ ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ሊጀመር ሰዓታት ሲቀሩት የከባቢ አየር አቀንቃኞችና ፖሊስ ተጋጩ። ፖሊስ በአየር ንብረት ለውጥ ድርድሩ የሚሳተፉ ባለስልጣናት ከአንዳች ተጨባጭ ስምምነት መድረስ ተስኖቸዋል ባሏቸው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞ ለማሰማት አደባባይ በወጡት አራማጆች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች በጽንፈኞች የሽብር ጥቃት መሰብሰብ በተከለከለበት የማዕከላዊ ፓሪስ በ ደ ላ ሪፐብሊክ አደባባይ እጅ ለእጅ በመያያዝ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ብቻ ሳይሆን ከዓርብ ዕለት አንስቶ በሺ የሚቆጠሩ የአየር ንብረት ተሟጋቾች በአውስትራሊያን፣ ፊሊፒንስ፣ ጃፓን እና ጀርመን አደባባይ በመውጣት የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ዘመቻ ጀምረዋል። ነገ ፓሪስ ላይ በሚጀምረው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የ 195 ሀገር ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ፤ « የሰው ልጆች ጠላት አሸባሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የከባቢ አየር ለውጥም ምክንያትን ሲሆን ተስተውላል ሲሉ ተደምጠዋል። ነገ በሚጀመረው የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ከአንዳች ስምምነት ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል።


እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ