ፓሪስ፤ የሽብር ሰለባዎችን አሰበች | ዓለም | DW | 10.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ፓሪስ፤ የሽብር ሰለባዎችን አሰበች

ፈረንሳይ በእስላማዊ ታጣቂዎች የተገደሉ የሽብር ሰለባዎችን በሕሊና ጸሎት ዛሬ አሰበች። የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ ፤ የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አኔ ሒዳልጎ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት በማዕከላዊ ፓሪስ በሚገኘው የደ ሪፐብሊክ አደባባይ በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓ.ም. በሽብር ህይወታቸውን ላጡ 150 ሰዎች ቋሚ መታሰቢያ ቆሟል።

በፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ እና የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አኔ ሒዳልጎ ይፋ በተደረገው ቋሚ መታሰቢያ «በዚህ ቦታ የፈረንሳይ ዜጎች በጥር እና ኅዳር የሽብር ሰለባ ለሆኑት ያላቸውን ክብር ይገልጣሉ» የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል። ፕሬዝዳንቱም ይሁኑ የፓሪስ ከተማ ከንቲባ ግን በስፍራዉ አንድም ቃል አልተናገሩም። ከመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ መጠናቀቅ በኋላ በቴሌቭዥን ንግግር ያደረጉት ከንቲባዋ ግን «ፓሪስ ፈርታለች። ይሁንና አሁንም በጽናት ቆመናል።» ሲሉ ባለፈው የጎርጎሪዮሳዊ አመት የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች በከተማዋ ላይ ያሳደሩትን ጫና አስታውሰዋል።

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ