ፓሪስ ከሽብር ጥቃቱ በኋላ | ዓለም | DW | 08.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ፓሪስ ከሽብር ጥቃቱ በኋላ

በፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ትናንት የተጣለዉን የአሸባሪዎች ጥቃት ተከትሎ የተለያዩ የዓለም መንግሥታትና ፖለቲከኞች ድርጊቱን በፅኑ ማዉገዛቸዉን ቀጥለዋል።

የፓሪስ ነዋሪዎችም ድርጊቱን በመቃወም ትናንት ምሽት በአደባባይ በነቂስ ወጥተዋል። ፈረንሳይ የትናንቱን የአሸባሪ ቅጣት ተከትሎ ፈረንሳይ ብሔራዊ የሃዘን ቀን ማወጅዋ ይታወቃል። በሌላ በኩል አንድ ሴት ፖሊስም ከየት መድረሱ ባልታወቀ ጥቃት መገደልዋ እንዲሁም ሁለት በፅኑ መቁሰላቸዉ ተነግሮአል። ዛሬ ፓሪስ እንዴት ዉላ ይሆን? ሌላ አንድ ፖሊስ የመገደልዋ ዜናስ እንዴት ነዉ? የፓሪስዋን ወኪላችንን ሐይማኖት ጥሩነህን አነጋግረናታል።


ሐይማኖት ጥሩነህን
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic