«ፍቅር ይበልጣል» | ባህል | DW | 24.02.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

«ፍቅር ይበልጣል»

ነዋሪነቱ ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ውስጥ ውስጥ ነው። ድምፃዊ ተረፈ አሰፋ ይባላል። የሌላኛው ድምጻዊ ገረመው አሰፋ ታናሽ ወንድም ነው። አዲስ ባዘጋጀው አልበሙ አላስፈላጊ ዘር ቆጠራ ውስጥ አንግባ፣ ከምንም በበላይ «ፍቅር ይበልጣል» ይለናል።

ድምፃዊ ተረፈ አሰፋ ኑሮውን ጀርመን ሐገር ላይ ከመሰረተ ወደ አስር ዓመት ገደማ ሆኖታል። ሶስት እህቶች እና አራት ወንድሞች አሉት። ከቤተሰብ በሙዚቃው የገፉት በተለይr እሱ እና ታላቅ ወንድሙ ገረመው አሰፋ ናቸው። ስለሙዚቃ ህይወቱ በማብራራት ይጀምራል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic