ፍራንሷ ኦሎንድ የፈረንሳዩን ምርጫ አሸነፉ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ፍራንሷ ኦሎንድ የፈረንሳዩን ምርጫ አሸነፉ

እሁድ ፈረንሣይ ውስጥ በተካሄደው ሁለተኛው ዙር የማጣሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሶሻሊስቱ ፍራንሱዋ ኦሎንድ አሸነፉ። የምርጫው ውጤት ፕሬዚደንት ኒኮላ ሣርኮዚይ ለተጨማሪ አምሥት ዓመታት በሥልጣን ላይ ለመቆየት የነበራቸውን ተስፋ አምክኗል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ

እሁድ ፈረንሣይ ውስጥ በተካሄደው ሁለተኛው ዙር የማጣሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ  ሶሻሊስቱ ፍራንሱዋ ኦሎንድ አሸነፉ። የምርጫው ውጤት ፕሬዚደንት ኒኮላ ሣርኮዚይ ለተጨማሪ አምሥት ዓመታት በሥልጣን ላይ ለመቆየት የነበራቸውን ተስፋ አምክኗል።  በይፋ በተገለፀው ውጤት መሰረት ኦሎንድ  52 በመቶ የመራጮች ድምፅ በማግኘት ነው ምርጫውን ያሸነፉት።  48 በመቶ ድምፅ ያገኙት ኒኮላ ሳርኮዚ  ሽንፈታቸውን በፀጋ ተቀብለዋል።  ሳርኮዚ ማምሻውን የምርጫው ውጤት ከተገለፀ በኋላ ለደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግር ለአሸናፊው ኦሎንድ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። በምርጫው ድምጽ እንዲሰጥ ጥሪ የተደረገለት ሕዝብ 45 ሚሊዮን ገደማ ይጠጋል። ከሁለት ሣምንት በፊት ተካሂዶ በነበረው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ፍራንሱዋ ኦሎንድ አይለው ሲገኙ የዝንባሌ መለኪያ መጠይቅ ውጤቶች የላቀ የማሸነፍ ዕድል የሚሰጡትም ለኚሁ ለሶሻሊስቱ ወገን ዕጩ ነበር።  ከ17 ዓመታት ወዲህ በፈረንሳይ አንድ ሶሻሊስት መሪ ስልጣን ሲይዝ ኦሎንድ የመጀመሪያው ናቸው። የመጨረሻው የፈረንሳይ ሶሻሊስት መሪ ፍራንሷ ሚቴሮ ነበሩ። የ57 ዓመቱ አዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ ከቀናት በኋላ ስልጣኑን በይፋ እንደሚረከቡ ተዘግቧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 • ቀን 06.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14qt5
 • ቀን 06.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14qt5