ፍራንስ ቴሌኮም የቴሌን የአስተዳደር ዘርፍ መረከብ | ኢትዮጵያ | DW | 22.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ፍራንስ ቴሌኮም የቴሌን የአስተዳደር ዘርፍ መረከብ

ከናይጀሪያ ቀጥሎ በአፍሪቃ በህዝብ ቁጥር ብዛት ሁለተኛውን ደረጃ የምትይዘው የኢትዮጵያ የቴሌኮምኒሽን አገልግሎት በኋላ ቀርነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ነው ።

default

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከ 80 ሚሊዮን ከሚልቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ 5 በመቶው የሚጠጋው ብቻ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ሲሆን በጎረቤት ኬንያ ግን የአገልግሎቱ ሽፋን ከሀምሳ በመቶ በላይ ነው ። በቴሌኮምኒኬሽን አገልግልት ድክመት በተደጋጋሚ ስሙ የሚነሳው የመንግስታዊው የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን አስተዳደራዊ ዘርፍ በአሁኑ ሰዓት በፈረንሳዩ ፍራንስ ቴሌኮም ኩባንያ እየተተካ ነው ። በዚሁ መሰረትም ኩባንያው ስራውን ተረክቦ መዋቅሩን በመዘርጋት ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና የኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ለዶይቼቬለ በሰጡት ቃለ እንዳስታወቁት የኮርፖሬሽኑን የአስተዳደር ዘርፍ ፍራንስ ቴሌኮም የሚረከበው የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት ለማቀላጠፍና አሰራሩንም ለማዘመን ነው ። ለውጡ የሚያስገኝውን ጥቅም እንዲሁም በአዲሱ ኩባንያ የቴሌ ሰራተኞች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ሚኒስትሩን ጠይቆ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ጌታቸው ተድላ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ