ፋህሚ አህመድና አዲሱ የሥራ መስክ | ባህል | DW | 01.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ፋህሚ አህመድና አዲሱ የሥራ መስክ

እንግዳችን የኤሌክትሪላል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ነው። በተማረበት ሙያ ሥራ አግኝቶ ነበር ይሁንና በፍላጎት ወደ ንግድ ሥራ ነው የገባው። ለምን? ስለዚህ ወጣት ማንነት እና ከሌሎች አራት ባልደረቦቹ ጋ ተደራጅቶ ስለሚሠራው ያስረዳናል።

ፋህሚ አህመድ መክር ይባላል። ተወልዶ ያደገው በምስራቅ ሐረርጌ- ሀሮማያ ወረዳ ነው። ወጣቱ በባህርዳር ዮንቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከተመረቀ በኋላ ለጥቂት ዓመታት ለኦሮሚያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ድርጅት አገልግሏል። ይሁንና ፋህሚ በሙያው ብዙ አልገፋበትም። በውስጡ ሌላ ምኞት ነበረው። ንግድ።«ፋህሚ እና ጓደኞቹ የስራ ማህበራት» ይሰኛል። አምስቱ ወጣቶች በጋራ የሚያንቀሳቅሱት የግል ስራ፤ ወጣቱ ዛሬ ስራ አስኪያች ሆኖ ያገለግላል። አምስቱ ባልደረባዎች ዛሬ ከእነሱ ሌላ ስምንት ሰዎች ቀጥረው ያሰራሉ። ለመሆኑ አምስት ውሳኔ ሰጪ ባለበት የስራ ህብረት ውስጥ ነገሮች እንዴት ይፈታሉ አልኩት? መፍትኼያቸውን ገልፆልናል።

ፋህሚ እና ጓደኞቹ በ2003 ዓ ም የጀመሩት ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና እየተስፋፋ እነሱም ስኬታማ እየሆኑ መሄዳቸውን የስራ አስኪያጅነት ድርሻ ያለው ፋህሚ ገልጾልናል። ሰሞኑን አንድ በስልክ የደረሰን አጭር የጹሁፍ መልዕክት ነበር። «አንድ ወጣት የፃፈልን ነው። « ኢትዮጵያ ለውጥ አሳይታለች ፤ስራ ፍጠሩ ይላሉ። ነገር ግን በዛው ልክ ግብር ይበዛል እንዴት ይሻለናል?» ይል ነበር መልዕክቱ። ፋህሚ ይህንን ሀሳብ ይጋራ ይሆን?

ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic