ፈንጂ ማምከንና ማፅዳት በአፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 05.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ፈንጂ ማምከንና ማፅዳት በአፍሪቃ

በአፍሪቃ በተቀበሩ ፈንጂዎች ሰብብ የሚደርሰውን ሞትና የአካል ጉዳት ለማስቆም ብቸኛው አማራጭ ሆኖ የተገኘውን ፈንጂዎች ማምከንና የማፅዳቱ ሥራ በስፋት እንደሚቀጥል የአፍሪቃ ህብረት አስታወቋል ።

በየአመቱ በአለም ዙሪያ በሺህዎችየሚቆጠሩሰዎች በተቀበሩ ፈንጂዎች ህይወታቸው ይጠፋል የአካል ጉዳትም ይደርስባቸዋል ። የዚህ ችግር ግንባር ቀደም ሰለባ ከሆኑት ክፍለ ዓለማት አንዷ አፍሪቃ ናት ። በአፍሪቃ በተቀበሩ ፈንጂዎች ሰብብ የሚደርሰውን ሞትና የአካል ጉዳት ለማስቆም ብቸኛው አማራጭ ሆኖ የተገኘውን ፈንጂዎች ማምከንና የማፅዳቱ ሥራ በስፋት እንደሚቀጥል የአፍሪቃ ህብረት አስታወቋል ። እስካሁን በዚህ ረገድ በአፍሪቃ ስለተከናወነውና ወደፊት ስለታቀደው የፈንጂ ማምከንና ማፅዳት እንቅስቃሴ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአፍሪቃ ህብረት ና የተመድ ሃላፊዎች ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር አገባ ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic