ፈረንሳይ ጥቃትና ምርጫ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ፈረንሳይ ጥቃትና ምርጫ

ስሙ በይፋ ያልተነገረ አንድ የ39 ዓመት ጎልማሳ ትናንት በከፈተዉ ተኩስ አንድ ፖሊስ ገድሎ፤ ሌላ አቁስሏል።እራሱም ተገድሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:06

 ፈርንሳይ ጥቃትና ምርጫ

ትናንት ማታ መሀል ፓሪስ ውስጥ በፖሊስ ላይ የተፈፀመው ግድያ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ላይ ጥላ አጥልቷል ። የመጀመሪያው ዙር የፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ሁለት ቀናት በቀሩበት በዛሬው እለት ከአራቱ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ሦስቱ ለዛሬ አቅደውት የነበረውን የምርጫ ዘመቻ ሰርዘዋል ። የዛሬው ዘመቻ የሰረዙት የቀኝ ፅንፈኛው ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን ፣ የመሀል አቋም ያላቸው ኤማኑኤል ማክሮ እና ወግ አጥባቂው ፍራንሷ ፊዮን ናቸው። ከመካከላቸው ለፔን ፈረንሳይ በአስቸኳይ የድንበር ቁጥጥር ተግባራዊ እንድታደርግ እና በአሸባሪ መዝገብ ውስጥ ስማቸው የሰፈረ የውጭ ዜጎች በሙሉ እንዲባረሩ ጥሪ አቅርበዋል ። የ39 ዓመቱ ማክሮ ደግሞ ህዝቡ በአደጋው እንዳይረበሽ እና አጋጣሚውን የሌሎች መጠቀሚያ እንዳያደርግ አሳስበዋል ። ትናንት ምሽት በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነበር በፓሪሱ ትልቅ ጎዳና በሾንዜሊዜ  አንድ ታጣቂ በአውቶማቲክ ጠመንጃ በፖሊስ መኪና ላይ ተኩስ ከፍቶ አንድ የፖሊስ መኮንን ገድሎ ሁለቱን ደግሞ ያቆሰለው ።ታጣቂው ከአካባቢው በእግሩ ለማምለጥ ሲሞክር ወዲያውኑ በአፀፋ ተኩስ ተገድሏል።ግለሰቡ ከተዋጊዎቹ አንዱ መሆኑን ራሱን እስላማዊ  መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ።የፈረንሳይ ባለሥልጣናት እንዳሉት የተገደለው 39 ዓመቱ ጥቃት አድራሹ ከፓሪስ ወጣ ባለ አካባቢ ነበር የሚኖረው ። ሌላ ያመለጠ ሁለተኛ ተጠርጣሪ ሳይኖር እንዳልቀረም ይገመታል። 

ኃይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች