ፈረንሳይ፤ በስደተኞች ጉዳይ ጠበቅ ያለ ረቂቅ ሰነድ አሳለፈች  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ፈረንሳይ፤ በስደተኞች ጉዳይ ጠበቅ ያለ ረቂቅ ሰነድ አሳለፈች 

በርካታ ስደተኞች ከሚጎርፉባቸዉ የአዉሮጳ ሃገራት መካከል አንድዋ የሆነችዉ ፈረንሳይ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች በሚመለከተ ጠበቅ ያለ የረቂቅ ዉሳኔ አሳለፈ።  በፓርላማዉ አብላጫ  ድምፅ  ያለዉ የኢማኑኤል ማክሮ ፓርቲ አንድ ግለሰብ የተቃዉሞ ድምፅ 14 ግለሰቦች ደግሞ ድምፅ ታቅቦ ማድረጋቸዉ ታዉቋል።

 

በአሳለፍነዉ የአዉሮጳዉያን 2017 ዓመት መጨረሻ ግድም የስደተኞችን እና ተገን ጠያቂዎችን ጉዳይ በተመለከተ የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ አስተዳደር ያወጣዉ አዲስ ረቂቅ እንዳይፀድቅ በርካታ ነቀፊታና ተቃዉሞ ገጥሞት ነበር። ይሁንና በያዝነዉ ሳምንት በጉዳዩ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት የተሰየመዉ የፈረንሳይ ምክር ቤት ከበርካታ ክርክርና ዉይይት በኋላ በ 228 ድምፅ ድጋፍ ፤ በ 139 ተቃዉሞ ሰነዱን አሳልፈዉታል። በፓርላማዉ አብላጫ  ድምፅ  ያለዉ የኢማኑኤል ማክሮ ፓርቲ አንድ ግለሰብ የተቃዉሞ ድምፅ 14 ግለሰቦች ደግሞ ድምፅ ታቅቦ ማድረጋቸዉ ታዉቋል። በፈረንሳይ  የብሔራዊ ግንባር ሊቀመንበር ማሪል ሎፔንን ጨምሮ የድጋፍ ድምፅ እንደሰጡበትም ታዉቋል።  የፓሪስዋ ዘጋብያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅታለች።    

ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ

ተዛማጅ ዘገባዎች