ፈረንሳይ በሲንቲዎች ላይ የጀመረችው ዘመቻ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ፈረንሳይ በሲንቲዎች ላይ የጀመረችው ዘመቻ

በየሀገሩ የተለያየ መጠሪያ አላቸው ፤ ጂፕሲ ሲንቲ ሮማ ትሲጎይነር ሲንጋሪ ይባላሉ ። ራሳቸውን ሲንቲ ሮማ ብለው የሚጠሩት እነዚህ ህዝቦች በአንድ ስፍራ ረግተው አይኖሩም ።

default

ተንቀሳቃሽ ህዝቦች ናቸው ። ከአያት ቅደመ አያቶቻቸው ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው ከዚህ ልምዳቸው ዛሬም አልተላቀቁም ። በተለያዩ የአውሮፓ ሐገራት ውስጥ ለዘመናት ቢኖሩም ከዘመነው አውሮፓ ጋር የሚመሳሰል ህይወት ግን የላቸውም ። የአብዛኛዎቹ ኑሮ ከ3ተኛው ዓለም ድሀ ህዝብ ጋር ይቀራረባል ። በየሚኖሩበት ሐገር የተገለለ ህይወት የሚገፉት እነዚህ ህዝቦች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ከአንዳንድ የምዕራብ አውሮፓ ሐገራት በግዳጅ እየተባረሩ ነው ። በቅርቡ ይህን መሰሉን ዕርምጃ በይፋ ከወሰዱት አገራት ውስጥ አንዷ ፈረንሳይ ናት ። ፈረንሳይ ባለፈው ሳምንት ህገ ወጥ ያለቻቸውን ሲንቲ ሮማዎች ወደ ሩሜንያ አባራለች ። ይህ የፈረንሳይ ዕርምጃም ከየአቅጣጫው ተወግዟል ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የአውሮፓ ህብረት ጭምር የፈረንሳይን መንግስት ድርጊት ተችተዋል ።

ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ