ፈረንሳይ ለፍፃሜው ደረሰች
ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2010ማስታወቂያ
ፈረንሳይ በዓለም ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ ለፍፃሜው ጨዋታ የቀረበችው በጎርጎሪዮሳዊው የዘመን ቀመር 2006ዓ,ም ጀርመን ላይ በተካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ጊዜ ነበር። ቡድኑ ለዚህ በመድረሱ ብቻ ሳይሆን በተጫዋዎቹ ብቃትም የተደሰቱት ፈረንሳውያን ትናንት ምሽቱን የፓሪስን ዋና ዋና ጎዳናዎች በሰንደቅ ዓላማቸው እና በርችቶች ታጅበው ደስታቸውን ገልጸዋል። ይህ የድል ስሜትም በመላው የፈረንሳይ ከተሞች መስተጋባቱን ፓሪስ የምትገኘው ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ በላከችው ዘገባ ጠቅሳለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ