ፈረንሳዩ ምሁር ከኢትዮጵያ ለምን ተባረሩ? | ኢትዮጵያ | DW | 21.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ፈረንሳዩ ምሁር ከኢትዮጵያ ለምን ተባረሩ?

ፈረንሳዊው ምሁር ሬኔ ለፎ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ህዳር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ አምርተው ነበር፡፡ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደደረሱ ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው በቀጥታ ወደ ፓሪስ መመለሳቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:51

ወደ ኢትዮጵያ እንዳልገባ የተከለከልኩት በኤምግሬሽን ኃላፊዎች ነው:- ሬኔ ለፎ

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚያቀርቧቸው ትንታኔያቸው ስማቸው ጎልቶ ይጠራል፡፡ ፈረንሳዊው ጸሀፊ ሬኔ ለፎ፡፡ ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት በፈረንሳይ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ በጥናት እና ምርምር ጽሁፎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሬኔ ለፎ ለበርካታ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለሱ ቆይተዋል፡፡ ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠየቁትን የስራ ቪዛ ካገኙ በኋላ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ ያመሩት ለፎ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ያልጠበቁት ነበር ያጋጠማቸው፡፡ በአየር ማረፊያ ከሚገኙ የኤምግሬሽን ኃላፊዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው በቀጥታ ወደ ፓሪስ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የላከችውን ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ፡፡

ሃይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ 
 

Audios and videos on the topic