ፀረ «አይ ኤስ» የኢራቅ ጦር ዘመቻ | ዓለም | DW | 02.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ፀረ «አይ ኤስ» የኢራቅ ጦር ዘመቻ

የኢራቅ ጦር በ«እስላማዊ መንግሥት፣ አይ ኤስ» አንፃር ግዙፍ ዘመቻ ጀመረ። ጦሩ በዚሁ ዘመቻው በ«አይ ኤስ » ቁጥጥር ስር የምትገኘዋን የቲክሪት ከተማ ነፃ የማውጣት ዓላማ አለው።

ጦሩ እንዳስታወቀው፣ ከመዲናይቱ ባግዳድ 170 ኪሎሜትር በስተሰሜን ርቃ በምትገኘዋ ቲክሪት ያሉትን የ«አይ ኤስ» ሠፈሮች በተዋጊ ጄቶች እና ሄሊኮፕተሮች ደብድቧል። ካለፉት የክረምት ወራት ወዲህ በኢራቅ እና በሶርያ ሰፊ መሬት በተቆጣጠረው የአክራሪዎቹ ሱኒዎቹ ቡድን «አይ ኤስ» አንፃር በሚካሄደው ዘመቻ ላይ ወ 30,000 የሚጠጉ ወታደሮች ተሳታፊዎች ናቸው። የኢራቅ ጦር በሀገሩ ሰሜናዊ ከፊል ከኩርዳውያኑ የፔሽመርጋ ተዋጊዎች ጋ ባንድነት በ«አይ ኤስ» አንፃር ጥቃቱን አጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቋል። ጦሩ የቀድሞው የሀገሪቱ መሪ ሳዳም ሁሴን ትውልድ ቦታ እና የ«አይ ኤስ» ጠንካራ ሠፈር የሆነችውን ቲክሪትን መልሶ ለመቆጣጠር ባለፉት ወራት ያካሄዳቸው ብዙዎቹ ጥቃቶች መክሸፋቸው ተገልጾዋል።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ