ፀረ ሕገ ወጡ የአልማዝ ንግድ ስብሰባ | አፍሪቃ | DW | 20.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ፀረ ሕገ ወጡ የአልማዝ ንግድ ስብሰባ

ውዝግብ ከሚታይባቸው አካባቢዎች በሚወጣ የአልማዝ ማዕድን ንግድ አንፃር የተጀመረውን ትግል የማጠናከር ዓላማ የያዘው በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ « ኬ ፒ ሲ ኤስ » በመባል የሚታወቀው « የኪምበርሊ ፕሮሰስ ሰርቲፊኬሽን ስኪም »

ቡድን ትናንት በደቡብ አፍሪቃ ጆሀንስበርግ ከተማ የአራት ቀናት ስብሰባ ጀመረ። ከ 81 ሀገራት የተውጣጡ ልዑካን ቡድኑ በሕገ ወጡ የአልማዝ ንግድ በተሰማሩ እና በሚገዙት አንፃር ጠንካራ ርምጃ መውሰድ በሚያስችለው የተሀድሶ ሀሳብ ላይ ይመክራሉ።
እአአ በ2003 ዓም የተቋቋመው « የኪምበርሊ ፕሮሰስ ሰርቲፊኬሽን ስኪም » ቡድን ፣ በምህፃሩ « ኬ ፒ ሲ ኤስ » ውዝግብ ከሚታይባቸው አካባቢዎች በሚወጣ የአልማዝ ማዕድን የሚደረገውን ንግድ ለማስቆም ጠንሮ ይታገላል። ይሁን እንጂ፣ ቡድኑ ከተመሠረተ ዛሬ ከአሥር ዓመታት በኋላም የአልማዙ ንግድ በአፍሪቃ የሚካሄዱ ውዝግቦች በቀጠሉበት ሂደት ላይ ሰፊ ድጋፍ እያበረከተ ይገኛል።
በስብሰባው መክፈቻ ላይ የተሰናባቿ የ« ኬ ፒ ሲ ኤስ » ሊቀ መንበር የደቡብ አፍሪቃ አምባሳደር ወሊሌ ንህላፖ ባሰሙት ንግግር፣ ተሳታፊዎቹ ልዑካን የቡድኑን ድክመት ለይተው በማወቅ ትግሉ የሚጠናከርበትን ዘዴ እንደሚጠቁሙ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
« ቡድኑ ውዝግብ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተመረተን አልማዝ በሚመዘግብበት ስራው፣ ከድህረ ውዝግብ በኋላ በነዚህ አካባቢዎች በሚነቃቃው የመልሶ ግንባታ እና የልማት ተግባርም ላይ ርዳታ ሊያቀርብ ይችላል። ለቡድኑ ትልቁ ፈተና የሚሆነው በሕገ ወጡ ንግድ አንፃር የጀመረውን ትግል ማጠናከር እና የሕዝቦችን ኑሮ ማሻሻል መቻሉ ነው። »

The logo of the Antwerp World Diamond Center (AWDC), one of the world's most important diamond-trading centres, is pictured on March 8,2010.

World Diamond Center Antwerpen


በብራስልስ የሚገኘው ለማዕድን ኩባንያዎች የሚሟገተው የአንትዎርፕ የዓለም የአልማዝ ማዕከል ፕሬዚደንት አቪ ፓዝ « ኬ ፒ ሲ ኤስ » ራሱን ሕገ ወጡን የአልማዝ ንግድ ለመታገል ለሚቀርቡ አዳዲስ ተሀድሶ ሀሳቦች ክፍት ማድረጉን አሞግሰዋል።
የዓለም የአልማዝ ማዕከል በ« ኬ ፒ ሲ ኤስ » ውስጥ የተነቃቃውን ተሀድሶ፣ እንዲሁም፣ አልማዙ በሚወጣባቸው እና በቀጥታ የርስበርስ ጦርነት በማይካሄድባቸው አካባቢዎች በሚኖሩት ማህበረሰቦች ላይ በሚፈፀመው የኃይል ተግባር አንፃር ትግሉን ማስፋፋቱን ጭምር ይደግፋል። »
ይሁን እንጂ፣ የሲቭሊ ማህበረሰብ ጥምረት ተወካይ የሆኑት ሻሚሶ ምትሲ የተሀድሶው ርምጃ አዝጋሚ ነው በሚል ወቀሳ ሰንዝረዋል። ምትሲ « ኬ ፒ ሲ ኤስ » ከሕገ ወጡ የአልማዝ ማዕድን ማውጣት ጋ በተያያዘ የሰብዓዊ መብት ረገጣ በሚካሄድባቸው ሀገራት ላይ ጠንካራ ርምጃ እንዲወሰድ ይፈልጋሉ። « ኬ ፒ ሲ ኤስ » በአልማዝ ማዕድናት ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ቁጥጥር ማድረግ፣ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን፣ ሻጮቹ እና ገዢዎቹን ለይቶ ማወቅ እንደሚጠበቅበት ነው ምትሲ ያመለከቱት። እንደሚታወቀው ፣ ኬ ፒ ሲ ኤስ » ዚምባብዌ የአልማዝ ማዕድንዋን እንድትሸጥ ፈቃድ ሰጥቶዋል፤ ይሁንና፣ ምቲሲ እንደሚሉት፣ ቡድኑ በዚችው ሀገር ማዕድኑ አልማዝ የሚወጣበትን አሰራር በተመለከተ ተጓድሎ ለሚገኘው ግልጽነት እና በኃላፊነት የሚጠየቅ ወገን ትኩረት አልሰጠም።


ይሁንና፣ የደቡብ አፍሪቃ የማዕድን ሚንስትር ሱዛን ሻባንጉ የምትሲን ሀሳብ አይጋሩትም።
« ኬ ፒ ሲ ኤስ » ዚምባብዌም የሚጠበቅባትን ማሟላቷን ካረጋገጥ በኋላ ነው ይህን ሂደት የጀመረው። በተለይ የአውሮጳ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣለውን ማዕቀብ በማንሳቱም ውሳኔአችን ትክክለኛ ነው ብለን እናምናለን። »
ስብሰባው የፊታችን ዓርብ በሚያበቃበት ጊዜ ደቡብ አፍሪቃ የሊቀመንበርነቱን ሥልጣን ለቻይና ታስረክባለች።

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic