ፀሀፊ ዳዊት ግዛው | ባህል | DW | 30.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ፀሀፊ ዳዊት ግዛው

አሁንም ሆነ በፊትም የሚጽፈው ለገንዘብ ሳይሆን የስነ ጽሁፍ ጥሙን ለማርካት መሆኑን የሚናገረው ዳዊት ከአሁን በኋላ የግጥም መፀሀፍ ለማሳተም አያስብም። ተጽፈው የተቀመጡ ሌሎች ድርሰቶቹን ግን በቅርቡ የማሳተም እቅድ አለው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:32

ፀሀፊ ዳዊት ግዛው

የሰለጠነበት እና የተሰማራበት ሞያ የኤሌክትሪክ ምህድስና ነው።ከርሱ ጎን ለጎን ደግሞ ይገጥማል ይጽፋል።ግጥሞቹንና እና አጫጭር ወጎቹን ያካተተበትን የመጀመሪያ መጸሀፉን በዚህ ዓመት  ለህትመት አብቅቷል። ለህትመት የተዘጋጁ ሌሎች ያልታተሙ የስነ ጽሁፍ ሥራዎችም አሉት፤የኤሌክትሪክ መሐንዲስ እና ጸሀፊ ዳዊት ግዛው።ትውልዱ እና እድገቱ ሐረር ለሆነው፣ ለዳዊት

 ስነ ጽሁፍ የታመቀን ስሜት ማውጫ ማስተንፈሻ ነው።ዳዊት እንደሚለው ከሥራው ጎን ለጎን ለሚያካሂደው የስነ ጽሁፍ ሥራ መሠረቱ የሐረሩ የልዑል ራስ መኮንን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ብራና የኪነጥበብ ማዕከል ነው።ከርሱ የቀደሙት የማዕከሉ አባላት የስነ ጽሁፍ ፍቅሩ ይበልጥ እንዲጨምር እና ይበልጡን ወደ ዘርፉ እንዲሳብ ምክንያት ሆኑኝ ይላል።ለስነ ጽሁፍ የላቀ ፍቅር እንዳለው የሚናገረው ዳዊት የተማረው የኤሌክትሪክ ምህድስና መሆኑ እና በዚሁም ሞያ መሰማራቱ ታዲያ ለምን የሚለውን ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም።ሰው በተሰኘውና ወደ 72 የሚሆኑ ግጥሞችን እና 5 ወጎችን በያዘው ባለ 105 ገጹ የዳዊት ግዛው መፀሀፍ «ኢትዮጵያ» እንደተባለው ግጥም ሁሉ ሌሎችም ሰው እና ሰውነት ላይ ያተኮሩ ግጥሞችም አሉ።ከመካከላቸው አንዱ «ፍሬ አልባ ማገዶ»የሚል ርዕስ የሰጠው ግጥሙ ነው። አሁንም ሆነ በፊትም የሚጽፈው ለገንዘብ ሳይሆን የስነ ጽሁፍ ጥሙን ለማርካት መሆኑን የሚናገረው ዳዊት ከአሁን በኋላ የግጥም መፀሀፍ ለማሳተም አያስብም። ተጽፈው የተቀመጡ ሌሎች ድርሰቶቹን ግን በቅርቡ የማሳተም እቅድ አለው።

ሙሉውን ዝግጅት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic