ጸረ-ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት | ዓለም | DW | 03.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ጸረ-ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት

አብዛኞቹ የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች ኔዘርላንድስ ዴን ሐግ የሚገኘውን ዓለም አቀፉን የወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አጥብቀው ይጠሉታል፤ ብሎም ይፈሩታል። በበርካታ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ነዋሪዎች ደግሞ ማንም ኾነ ማን ከፍርድ ሒደት እንዳያመልጥ ጥብቅ ፍላጎት አላቸው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:32
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:32 ደቂቃ

ኬንያ እና «አይ ሲ ሲ»

በዘር እና በፖለቲካ ሳቢያ ተቃዋሚዎቻቸውን አሳደው የሚገድሉትን የአፍሪቃ አንዳንድ መሪዎችን እንዲሁም ባለሥልጣናትን ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስካሁን ከሷል። የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ «ይኽ ከእግዲህ ማክተም አለበት» ሲሉ ጥሪያቸውን አዲስ አበባ ለስብሰባ በተገኙበት አሰምተዋል። የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት የፕሬዚዳንቱን ንግግር «አደገኛ አኪያሄድ» በሚል ተቃውመውታል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጉዳዩን ተከታትሎ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic