ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች ጥናት በጀርመን | ባህል | DW | 03.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች ጥናት በጀርመን

ጀርመን የኢትዮጵያ ባህል ቋንቋ ጥናት በአዉሮጳ እንዲጀመር ያደረገች የመጀመርያዋ አዉሮጳዊት ሀገር መሆንዋ ይታወቃል።

በሀንቡርግ ዩንበርስቲ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ጥናት የትምርት ክፍል በአፍሪቃ ቋንቋዎች እና ባህሎች ላይ ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የአማርኛ የግዕዝ አልፎ አልፎ የትግርኛ እና የኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት ይሰጣል። በኢትዮጵያ የብራና ጽሑፎች ላይ ጥናትና ምርምር ይካሄዳል። በጀርመን ሀንቡርግ ከተማ በሚገኘዉ የአፍሪቃ በተለይም በኢትዮጵያ ጥናት የትምህርት ክፍል ዉስጥ በምርምር ሥራና የPHD ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ ያሉት አቶ አብርሃም አዱኛ በዕለቱ ዝግጅታችን ጋብዘናል።

የኢትዮጵያ ጥናት በጀርመን ብሎም በአዉሮጳ የጀመረዉ በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን በጀርመናዊዉ ተመራማሪ ሂዩብ ሩዶልፍ ነዉ። ጀርመናዊዉ ተመራማሪ ሂዩብ ሩዶልፍ ከአባ ጎርጎሪዮስ የአማርኛና የግዕዝ ቋንቋዋን በመማራቸዉም በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ብዙ ሰርተዋል፤ ከ 17 ኛዉ ክፍለ ዘመን የጀመረዉ የኢትዮጵያ ጥናት በተለይ በሀንቡርጉ ዩንቨርስቲ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። በኢትዮጵያ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎች ላይ ከተለያዩ የአዉሮጳ ምሁራን ጋር በሀንቡርግ ዩንቨርስቲ ጥናት የሚያደርጉት አቶ አብርሃም አዱኛ፤ ስለ ጥንታዊዉ የኢትዮጵያ የብራና ጽሑፍ ከኢትዮጵያዉያን ይልቅ ምዕራባዉያኑ ያዉቁታል ከፍተኛ ምርምርም አድርገዉበታል፤

በአዉሮጳ ሕብረት የሳይንስ ተቋማት የሚደገፈዉ የኢትዮጵያ ጥንታዊ የብራና ፅሁፎች መዘርዝር የመሥራት ማለትም ካታሎግ የማድረግ ፕሮዤ ላይ በጀርመን ሐንቡርግ ዮንቨርስቲ ዉስጥ የሚሳተፉት የዕለቱን እንግዳ አቶ አብርሃም አዱኛን እናመሰግናለን። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫዉን በመንካት ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic