ጥቅምት፤ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ወር | ጤና እና አካባቢ | DW | 17.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ጥቅምት፤ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ወር

በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን አቆጣጠር በየዓመቱ ከጥቅምት 1 እስከ 31 ድረስ በመላዉ ዓለም ለኅብረተሰቡ ስለጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በመሆን ይታወቃል። ሰዎች ቅድመ ምርመራ ማድረጋቸዉ በሽታዉ ስር ሳይሰድ መታከም እንዲችል እንደሚረዳ የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች አዘዉትረዉ ይመክራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:03
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
11:03 ደቂቃ

በየወሩ ራስን መመርመር ይመከራልል፤

 የዓለም የጤና ድርጅት በቅርቡ ይፋ እንዳደረገዉ በየዓመቱ 1,38 ሚሊየን አዳዲስ የጡት ካንሰር ታማሚዎች በመላዉ ዓለም ይገኛሉ። በተመሳሳይም በዚሁ ምክንያት በየዓመቱ 458 ሰዎች ይሞታሉ። የጡት ካንሰር በበለፀጉትም ሆነ በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገራት ሴቶችን የሚያጠቃ የካንሰር አይነት መሆኑንም ድርጅቱ ያመለክታል። እንደድርጅቱ መረጃ ከሆነም በከተሞች መስፋፋት እና የምዕራቡን ዓለም የኗኗር ስልት በመቅዳት ምክንያት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸዉ ሃገራት የካንሰር ታማሚዎች ቁጥር ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ እየጨመረ መሄዱ እየታየ ነዉ።  የዓለም የጤና ድርጅት አክሎም በአሁኑ ወቅት የጡት ካንሰርን የሚያስከትለዉ ይህ ነዉ የሚባል በቂ ምክንያት እንደሌለ፤ አስቀድሞ የሚደረግ ምርመራም በሽታዉን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዋነኛ ስልት መሆኑንም አፅንኦት ሰጥቶ ያሳስባል።

በመላዉ ዓለም በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት ወር አንድ ብሎ እስኪሰናበት ድረስ ስለጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ እና በግል ሊወሰድ ስለሚገባ ምርመራም ሆነ ጥንቃቄ መረጃዎች በሰፊዉ ይሰራጫሉ። ኢትዮጵያም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመረች ዘንድሮ 11ኛ ዓመት እንደሞላት የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ ይጠቁማል።

Gesundheit Gesundheitswesen Medizin Früherkennung Brustkrebs (Fotolia/Forgiss)

«የጡት ካንሰር በሽታን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነዉ! ጡትዎን በመዳሰስ ቅድመ ምርመራ በማድረግ ሕይወትዎን ይታደጉ!» በሚል መሪ ቃል በያዝነዉ የጥቅምት ወር ለኅብረተሰቡ ስለካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ ያሰፈረዉ መረጃ ያመለክታል። ሰዎች ስለበሽታዉ እንዲያዉቁ፤ የታመሙና አቅም የሌላቸዉ ወገኖች ደግሞ ህክምና እንዲያገኙ የበኩላቸዉን የሚያደርጉ ጥቂት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተንቀሳቀሱ ነዉ። በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለዉን የግንዛቤ ደረጃ እንዴት ይመዝኑታል? ሙሉ ቅንብሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic