ጥቃቶች በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች | ዓለም | DW | 19.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ጥቃቶች በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች

ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ባሳለፍነዉ ሳምንት ማለቂያ ተከታትለዉ የደረሱት ጥቃቶች የሀገሪቱን የፀጥታ ጥንቃቄ ጥያቄ ላይ እንደጣለዉ ነዉ የሚነገረዉ። ኒዉ ዮርክ፣ ኒዉ ጀርሲ እንዲሁም ሚኒሶታ ዉስጥ በደረሱ የፍንዳታ እንዳ በስለት የመዉጋት ጥቃቶች በርካቶች ተጎድተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

ጥቃት በዩኤስ

የተመድን ዓመታዊ ስብሰባ በምታስተናግደዉ ኒዉ ዮርክ ከተማ ቅዳሜ ምሽት የደረሰዉ ፍንዳታ 29 ሰዎችን ለጉዳት መዳረጉን፤ በሚኒሶታዉ የስለት ጥቃትም ዘጠኝ ሰዎች ተጎድተዉ ሃኪም ቤት ገብተዋል። የኒዉ ዮርኩ ፍንዳታ ጥቃት የሽብር ድርጊት መሆኑን የሚናገሩት የከተማዋ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ ትስስር እንዳለዉ ግን አላረጋገጡም። ሆኖም 1ሺህ ተጨማሪ የፖሊስ እና የልዩ ጥበቃ ኃይል ተሠማርቷል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic