ጥቃት በማእከላዊ ጎንደር | ኢትዮጵያ | DW | 30.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጥቃት በማእከላዊ ጎንደር

ታጣቂዎቹ የተሳፋሪዎችን መታወቂያቸውን እያዩ በመለየት 6ቱን እንደገደሏቸው አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ከጥቃቱ በኋላም የጎንደር ከተማና አካባቢው ወጣቶች ዛሬ ጠዋትና ትናንትና ወደተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወስዱ ዐቢይ መንገዶችን በደንጋይ ዘግተው እንደነበር እና አንድ ሆቴል እንዳወደሙ የዓይን እማኙ ለዶየቼ ቬለ ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:34

በማእከላዊ ጎንደር ጥቃት 6 ተገደሉ

በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትናንት ጠዋት ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በመኪና ይጓዙ በነበሩ ሰዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን መንግስትና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ ትናንትና ጠዋት ከጭልጋ ወደ መተማ በሚጓዝ ተሸከርካሪ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ግንት በተባለ ቦታ ላይ ታጣቂዎቹ የተሳፋሪዎችን መታወቂያቸውን እያዩ 6ቱን ለይተው እንደገደሏቸው አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ከጥቃቱ በኋላም የጎንደር ከተማና አካባቢው ወጣቶች ዛሬ ጠዋትና ትናንትና ወደተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወስዱ አቢይ መንገዶችን በደንጋይ ዘግተው እንደነበር እና አንድ ሆቴል እንዳወደሙ የአይን እማኙ ለዶየቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከጥቃቱ በኋላ ደረሰ ስለተባለው ግጭት ዝርዝር የምርመራ ውጤት እንዳልደረሰው ለዶቼቬለ አስታውቋል። ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር ዝርዝር ዘገባ አለው።
አለምነው መኮንን 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ  

Audios and videos on the topic