ጥቃትና መፈናቀል በአማሮ ልዩ ወረዳ | ኢትዮጵያ | DW | 14.05.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ጥቃትና መፈናቀል በአማሮ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌያት የታጠቁ ሀይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ከስድስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቀሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29

ከስድስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌያት የታጠቁ ሀይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ከስድስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቀሉ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ነዋሪዎቹ ከትናንት ጀምሮ አካባቢያቸውን እየለቀቁ የሚገኙት ትናንት ለሊት ወደ መንደሮቹ ዘልቀው የገቡ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው ሌሎች ሁለት ማቁሰላቸውንና የመኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን ተከትሎ ነው። ታጣቂዎች በየጊዜው በልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ላይ የሚደርሱት ጥቃት እየተባባሰ ይገኛል የሚሉት የወረዳው ባለስልጣናት በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ አልቻለም ሲሉ ወቅሰዋል ።

 

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic