ጥምረት ለህይወት ኢትዮጵያ | ባህል | DW | 18.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጥምረት ለህይወት ኢትዮጵያ

ጥምረት ለህይወት ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። በተለይ ወጣትና ጎልማሳ እናት ኢትዮጵያውያንን በድርጅቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጥናል።

ጥምረት ለህይወት ኢትዮጵያ   በብዛት ከውጭ ሀገር በሚገኝ ድጎማ ይንቀሳቀሳል።

ድርጅቱ ከተመሰረተ ስምንት አመት ሊሆነው ነው። በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በርካታ ሴቶችን ሰብስቦ በሙያ ያሰለጥናል። አቶ ተፈራ አለሙ፤ የፕሮግራም አስተባባሪ እንዲሁም ድርጅቱን ከመሰረቱት አንዱ ናቸው። ስለድርጅቱ አላማ  አጫውተውናል።

እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በስልጠና ላይ የሚገኙት መሰረት በቀለ  እና  በቀለች ደበሌም ስለ ስልጠናቸው ገልፀውልናል። ለሰልጣኞቹ የወደፊት የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ከሚጥሩት አንዱና የስልጠና ክፍል ኃላፊ የሆነው መስፍን ክፍሌ የበኩሉን ብሎናል።

ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic