ጤዛ፣ ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት! | ባህል | DW | 31.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጤዛ፣ ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት!

ባለፈዉ እሁድ ምሽት ላይ ነዉ። የሁለት ሽህ ታሪክ እንዳላ በሚነገርላት በኮለኝ ከተማ በኢትዮጽያዊ ታዋቂ የፊልም ሰሪ የተቀናበረዉ ፊልም ጤዛ ለተመልካች ቀርቦአል።

default

ፊልም ኢኒሳቲቨ ተብሎ በሚጠራዉ ጀርመናዊዉ ድርጅት በተለይ አፍሪቃ ጠቀስ ፊልምን በማምጣት ለህዝብ ያቀርባል። የፊልም አቀናባሪዎችንም በማጋበዝ ለህዝብ ለተማሪዎች ስለ ፊልሙ ትንተና እንዲያደርጉ ይጋብዛል። አድማጮች በለቱ ተገኝተን ጤዛን ፊልምን ተከትለን እዉቁን ኢትዮጽያዊ የፊልም ስራ አዋቂ ፕሮፊሰር ሃይሌ ገሪማን አነጋግረን በዛሪዉ ጥንቅር ይዘን ቀርበናል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ
እዉቁ የፊልም ስራ አዋቂ ፕሮፊሰር ሃይሌ ገሪማ በኢትዮጽያ ሳይሆን በአለም ታዋቂ ከሚባሉት የፊልም ስራ አዋቂዎች አንዱ መሆኑ ተገልጾአል። በተለይ በቅርቡ ማለት ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት ጤዛ በተሰኘዉ ፊልሙ ታዋቂ በሆነዉ የአፍሪቃ ፊልም ፊስቲቫል በዋጋዱጉ ሽልማትን አግኝተዋል፣ ባለፈዉ ሳምንት ፕሮፊሰር ሃይሌ ይህንኑ ስራዉን ይዘዉ ወደ ጀርመን የመጣዉ በግብዣ ነዉ። ለሁለተኛ ግዜ ፊልሙ ለህዝብ እንዲታይ የፊልም ስራ እዉቀታቸዉን ለወጣት የፊልም ስራ ተማሪዎች ትምህርት እና ትንተና እንዲሰጥ ነዉ። በኮለኝ እንብርት ላይ ባለዉ አነስ ባለ ሲኒማ ቤት ዉስጥ ህዝብ ተሰብስቦአል፣ የፊልም ስራ አዋቂዉ ፕሮፈሰር ሃይሌ ገሪማ፣ ጀርመንኛ ወደ እንግሊዘኛ የሚተርጉምለትን እና የፊልም ኢኒሳቲቨ ቢሮ ስራ አስኪያጅን መድረክ ላይ ይዞ ወጣ ሃይሌ ገሪማን ለማየት የጓጓዉ ታዳሚ ደስታዉን እንኻን ደህና መጣህ በማለት በጭብጨባ አስተጋባለትጤዛ ፊልም በኮለኝ ለሁለተኛ ግዜ ነዉ የታየዉ በህዝብ ጥያቄም በየፊልም ቤቱ ለመታየት እቅድ ላይ መሆኑ በመገለጽ ላይ ነዉ። በኢትዮጽያችን በአማርኛ የተቀናበረዉ ይህ ፊልም በከፊል በኮለኝ ከተማ ዉስጥ ነዉ የተቀረጸዉ። በኮለኝ የፊልም ኢኒሳቲቨ ተጠሪ በመቀጠል፣ በኮነኝ ባለዉ የፊልም ስራ አካዳሚ ፕሮፊሰር ሃይሌን ተማሪዎችን እንዲያስተምር ስለጋበዘዉ እኛም ፊልሙን በድጋሚ ለማየት እድሉ እንዳያመልጠን በማሰብ ዛሪም ይዘነዉ ቀርበናል እንኳን ደህና መጣህ ሲል ደስታዉን በድጋሚ ገልጾአል። ፕሮፊሰር ሃይሌ ገሪማም በማስስገን በኮለኝ ዳግም መገኘቴ ደስታ ይሰማኛል፣ ምክንያቱም፣ በመጀመርያ የፊልሙን አንድ ክፍል ተዉኔት እዚህ ከተማ በመቅረጻች፣ ሌላዉ የምዕራባዊዉ ጀርመን መገናኛ ተቋም በጀርመንኛ ምህጻሩ የ WDR ዋና መስሪያ ቤት እዚህ በመሆኑ ነዉ።

Äthiopien Regisseur Haile Gerima

ፕሮፊሰር ሃይሌ ገሪማ

ስሄድ አገኝኋት ስመለስ አጣኋት ይላል ሁለት ሰአት ከሃያ ደቂቃ የሚዘልቀዉ ጤዛ የተሰኘዉ ፊልም በኢትዮጽያ ቀድም ባለዉ ግዜ የነበረዉ የዘዉድ አስተዳደር ወድቆ በምትኩ በሶሻዝም ስር የሚተዳደረዉ የግዜያዊዉ ወታደራዊዉ አገዛዝ ስር የነበረዉን የህዝብ ስቃይ የአገር ስቃይ አጉልቶም ያሳያል። ወታደራዊዉ ስርአት ስልጣን ይዞ በስሩ የነበረዉ ጎራ መፍቀረ ምስራቅ ፍልስፍና የእርስ በርስ አለመስማማት ከዝያም ስርአቱ ያካሂድ የነበረዉ ርዕዮተ አለም ህዝቡን ለስቃይ አገሪቱን ለድህነት ለችግር ለሰቆቃ መዳረጉን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

በአፍሪቃ የፊልም ፉስቲቫልን ሽልማትን በቡርኪና ፋሶ ዋጋዱጉ፣ ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ 2009 አ.ም ያገኘዉ ጤዛ ፊልም በጣልያን በቬኔዲሽ እንዲሁም በቱኒዝያ የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘቱ ተገልጾአል። የፊልም ዋና አዘጋጅ ሃይሌ ገሪማ ይህንን ጤዛ የተሰኘዉን ፊልም የሰራሁት ስለ ደርግ አስተዳደር ገጽታ ለመግለጽ ሳይሆን ይላል፣ በደርግ ስርአት የነበርኩት አሜሪካን ነበርኩና፣ ይህንን ፊልም የሰራሁት በአፍሪቃ ምድር ላይ የሚታየዉን የጭቆና፣ ፍትህ አልባነት ለማሳየት ነዉ። የህግ የበላይነትን በሌለበት ስርአት የሚደርሰዉን ስቃይ ለማሳየት ነዉ ሲል ገልጾአል። በጤዛ ፊልም ስልጣን የያዘዉም ሆነ ተቃዋሚዎች በተጨባጭ ሁኔታ በአገሪቷ ሰላም ፍትህ የሞላበት ስርአትን ለማምጣት በትክክለኛዉ መንገድ አልተጓዙም።

በዚህም ትኩስ ጉልበት ትኩስ አዕምሮ እና ትኩስ እዉቀት ያላቸዉ ኢትዮጽያዉያን በስርአቱ ብልሹነት አገሪቷን ሊገነቡዋት ሊኖሩባት አልቻሉም። ከምዕራቡ አለም የከፍተኛ ትምህርታቸዉን ተምረዉ ወደ አገራቸዉ የተመልሱ ኢትዮጽያዉያንም፣ እዉቀታቸዉን ለወገናቸዉ ማከፈል አለቻላቸዉን ፊልሙ በግልጽ አስቀምጦታል።

ጤዛ ፊልም ዉስጥ የቢቢሲ ራድዮ መግለጫ እንደዘገበዉ በደርግ ስርአተ ፍጻሜ ዋዜማ ላይ የነበረዉን ሁኔታ ደርግን የተኩት ወገኖች የአልባንያዉያን አይነት ሶሻሊዝም እንደሚከተሉ መግለጹን የሚያሳይ ተዉኔትም በፊልሙ ተካቶአል። ፊልሙ የበርሊኑ ግንብ ሲፈርስ እንዲሁም በቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመን ጠንከር ብሉ ይታይ የነበረዉንም የዘር ጥላቻ አስቀምጦታል። ያም ሆነ ይህ ጤዛ በንጹህ ልቦና ከመገዳደል ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ስርአትን ለማምጣት በስነ-ምግባር እና በትምህርት የታነጹ ብርሃንን ሰንደቃቸዉ ያደረጉት ከአገሪቷ ማህጸን የሚወጡት ታዳጊ ህጻናት መሆናቸዉን በማመላክት በተስፋ ትረካዉን ይገታል።
የፊልም ስራ አዋቂዉ ሃይሌ ገሪማ በመግብያዉ ላይ እንደገለጸዉ በፊልሙ ገሚሱ ትወና በትወለደባት ገጠር ዉስት እንደተቀረጸ ተዋናዮቹም ቤተሰቦቹ ዘመዶቹ መሆናቸዉን ሳይጠቅስ አላለፈም። ታድያ ይላል ፕሮፊሰር ሃይሌ ገሪማ እንደሚመስለኝ በኢትዮጽያ ትኩሱ ሃይል ያለዉን የፊልም ስራ በተቻለዉ ለመሻሻል ተግቶ እየሰራ ይመስለኛል፣

ጓሼ ሃይሌ አልኩት በመቀጠል የሰራኸዉ ፊልም ትልቅ የታሪክ ማህደር ነዉ፣ ከታሪኩ ባሻገር ባህላችንንም ለዉጭዉ አለም የሚያሳይ ይመስለኛል አልኩት መልሱ «ታሪክን ለሰዉ ከማሳወቃችን በፊት እኛ እራሳችን አጥርተን እራሳችን ማወቅ አለብን ለልጆቻችንም ማሳወቅ አለብን....»

Burkina Faso Ouagadougou Fespaco-Schild

ሃይሌ ገሪማ በጀርመን ቆይታዉ ቀኑን የፊልም ስራ ትምህርት በመስጠት ምሽት ላይ ለፊልሙ ትንተና ሲያደርግ ከከተማ ከተማ ሲሯሯጥ ነዉ የሰነበተዉ። ጤዛ ፊልም ገሚሱ በጀርመን መቀረጹ በጀርመን ስላለዉ የዘር መድሎ መተወኑ ጀርመኖችን አላስቆጣም ሌላዉ ጥያቄ ነበር « ጀርመኖች ፊልሙን በደስታ ነዉ የተቀበሉት እንደዉም፣ በተለያዩ ከተሞች ባሉ ፊልም ቤቶች እንዲታይ ጥያቄ ቀርቦአል፣ በቅርቡ በየፊልም ቤቶቹ መታየቱ አይቅርም»

ጀርመናዉያን በፊልሙ እንደተደሰቱ በርግጥ የፊልሙ ታዳምያን ገልጸዋል፣ ኢትዮጽያዉያንስ «ፊልሙ በአገራችን የነበረዉን አንድ አስከፊ ስርአተ ማህበር ምን ሁኔታ እንደ ነበር ያሳያል፣ ፊልም ሰሪዉ ትረካዉን ጥሩ ሰርቶአል ተዋቶለታልም»

በፊልሙ መጠናቀቅያላይ አንጋፋዉ ኢትዮጽያዊ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ እናት ለምንትሙት እያለ ሲያዜም ተካቶአል። ጤዣ በኢትዮጽያችን ታሪክ አንድ ትዉልድ የጠፋበት ዘመን በማህደር አስቀምጦ ሲያሳየን፣ በሌላ በኩል ተማሪዉ ምሁሩ ገበሪዉ ቄስ ህጻን እናት አዋቂዉ ባህሉን ይዞ ሲራመድ ያሳየናል፣ ፕሮፊሰር ሃይሌ ገሪማን ድንቅ አድርጎ ለሰራዉ ፊልሙ እናመሰግናለን።
አዜብ ታደሰ